tgoop.com/sealite_mehret/5678
Last Update:
🕊
እንኩዋን ለበዓለ ዕለተ "ቶማስ ወአብርሃም" ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ልክ የሰሙነ ሕማማቱ ዕለታት ስምና ምሥጢር እንዳላቸው ሁሉ ከትንሳኤ በሁዋላ የሚገኙ ዕለታትም ስምና ምሥጢር አላቸው::
ሰኞን ቤተ ክርስቲያን "ማዕዶት" ብላ እንደምታከብር ትናንት የተመለከትን ሲሆን ማክሰኞን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን "ቶማስ" : አንድም "አብርሃም" ብላ ታከብረዋለች::
፩. 🕊 † ቶማስ † 🕊
ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ሲሆን ለጊዜው ትንሳኤ ሙታንን ከማያምኑ ሰዱቃውያን ወገን በመሆኑ የክርስቶስን ትንሳኤ ተጠራጥሮ ነበር::
ምሥጢሩ "ግን ካላየሁ : ካልዳሰስኩ አላምንም" ያለው ከፍቅሩ የተነሳ እውነት አልመስልህ ብሎት ነው::
አንድም ጌታ መለኮታዊ ጎኑን እንዲዳስሰው ቢፈቅድለት ነው:: ይህች የቅዱስ ቶማስ እጅ ዛሬ ድረስ ሕያው ናት:: ተአምራትንም ታደርጋለች::
፪. 🕊 † አብርሃም † 🕊
ከጻድቃነ ብሊት [ብሉይ] አንዱ የሆነው አባታችን አብርሃም ከጽድቁ የተነሳ ርዕሰ አበው [የአባቶች አለቃ] ተብሏል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃም ፈጣሪ ሲሆን የአብርሃም ልጅ መባልን ወዷልና::
በተለይ በከበረ ትንሳኤ የምናገኛትን መንግስተ ሰማያት በስሙ [የአብርሃም ርስት ተብላ] ተጠርታለችና አባታችን በዚህ ቀን ይታሰባል::
እግዚአብሔር ከ፪ቱ ታላላቅ ቅዱሳን ጸጋ በረከትን ያድለን::
"✞" እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ። በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ ፥ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ ፥ በራሱ ማለ ፤ እንዲሁም እርሱ ከታገሰ በኋላ ተስፋውን
አገኘ።
ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥ ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ፥ የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ ፥ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር ፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፡፡ "✞" [ዕብ. ፮:፲፫]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
BY ⛪ ሰዐሊተ ምህረት ⛪ (የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምስሎች)
Share with your friend now:
tgoop.com/sealite_mehret/5678