tgoop.com/sealite_mehret/5681
Create:
Last Update:
Last Update:
🔔
[ በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ ! ]
፩. የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ታላላቅ መንፈሳዊ በዓላትን በተለይም የልደትንና የፋሲካን በዓላት እየጠበቁ የዘፈን ኮንሰርት የሚያዘጋጁ አካላት ዛሬም ከዚህ ግብራቸው ሊታረሙ አልፈቀዱም።
[ ሰይጣን ምዕመናንን ከገቢረ ጽድቅ ወደ ገቢረ ኃጢዓት ፣ ከብርሃናዊው መንፈሳዊ ሕይወት ወደረከሰው የጨለማ ጥፋት ለመውሰድ የጾሙን መፈታት በተጠንቀቅ ሲጠባበቅ ቆይቶ ወደ ዳንኪራው መጣራቱን ተያይዞታል። ]
" በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ።" [ ኢሳ.፲፫፥፳፩ ]
፪. በዐቢይ ጾም ክፍት የነበሩ ስጋ ቤቶችን መላው ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በየአካባቢው ሲታዘብ ሰንብቷል። እነዚህ በኦርቶዶክሳዊ ማልያ የሚንቀሳቀሱ አሕዛባዊ የረከሱ የስጋ መሸጫ ቤቶች ክርስቲያናዊ መስለው ለመታየት ሰሙነ ሕማማትን ሱቃቸውን ዘግተው የማታለልና የማጭበርበር ተግባርን ሲፈጽሙ ተስተውለዋል።
[ በሃይማኖት የሚኖር ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሁሉ በዐቢይ ጾም [ በአዋጅ አጽዋማት ] ስጋ ሲሸጡ ከነበሩና ዛሬም በክርስትና ማልያ ሊያታልሉ ከሚሞክሩ የረከሱ [የአሕዛብ] ሱቆች በመራቅ ሃይማኖቱን ሊጠብቅ ይገባል። ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
BY ⛪ ሰዐሊተ ምህረት ⛪ (የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምስሎች)
Share with your friend now:
tgoop.com/sealite_mehret/5681