tgoop.com/sew720/1167
Create:
Last Update:
Last Update:
አንድ ቀን አንዲት የትምህርት ቤት አስተማሪ ከታች ያለውን ቁጥር በሠሌዳ ትፅፈዋለች...
9×1=7😛
9×2=18
9×3=27
9×4=36
9×5=45
9×6=54
9×7=63
9×8=72
9×9=81
9×10=90
ፅፋ ስትጨርስም ዞር ብላ ተማሪዎቹን ትመለከታለች። ተማሪዎቹ ሁላቸውም በሷ ሲስቁ ታያቸዋለች።
ምክንያቱም የመጀመርያው ስህተት ስለሆናበቸው ነው።
ከዛም አስተማሪዋ የሚከተለውን ትላቸዋለች።
የመጀመረያውን ስህተት የፃፍኩት ሆን ብዬ ነው ምክንያቱም እናንተ አንድ ነጥብ እንድትማሩ ስለፈለኩ ነው።
አለም እናንተን እንዴት እንደምታስተናግድ እንድታውቁ ይህ ለናንተ ነው።
ትክክል የሆነውን ዘጠኝ ጊዜ ስፅፍ አይታችሁኛል ነገርግን አንዳችሁም አላማሰገናቹኝም
ስለሰራሁት አንድ ስህተት ግን ሁለችሁም ሳቃቹብኝ
ትምህርቱ ይሄ ነው👉
አለም ስለሠራችሁት አንድ ስህተት ትቀጣችኋለች፤ ነገርግን ደጋግማችሁ ለሠራችሁት መልካም ነገር ላታመሠግናችሁ ትችላለች።
ስለዚህ ተስፋ እንዳትቆርጡ ! !
👉ሁሌም ከትችቶች የፀዳን እንሁን!
ከተቻለ መልካም ስራዎችን እናበረታታ
@sew720
BY የ ዕውቀት ምንጭ
Share with your friend now:
tgoop.com/sew720/1167