tgoop.com/tdarna_islam/4563
Last Update:
🍂ጣፋጭ መሳዩ መርዝ የሃራም ፍቅር!
ይሄ ነገር በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው። በጣም የሚገርመው ዛሬ ላይ ብዙ ወጣቶች የተዘፈቁበት ጉዳይ ሆኗል። አላህ ካዘነላቸው ውጪ ቂርአታቸው ላይ ጠንካራ የሆኑ፣ መድረሳ የሚከታተሉ ሁሉ ሳይቀር ለወደፊቱ እንጋባለን በሚል አጉል ተስፋ የሀራም ፍቅር ይጀምሩና መሀል ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ይቋረጣል፤ ታድያ በዚህ ጊዜ ሴቷ ሌላ ወንድ ለሃላል ፈልጓት ቢመጣ እንኳን ከመጀመሪያው ጋር በሀራም ፍቅር የደራ ወሬ ስለጀመረች ለኒካህ ቆርጦ የመጣውን እሺ አትልም። የሚገርመው ያኛው እንደማያገባት እያወቀች ሁሉ ቆረጦ ለመጣው መልሷ እንቢታ ይሆናል። እሺ ብላ ብታገባው ራሱ ቀልቧ ሁሉ ከመጀመሪያው በሀራም ስታወራው ከነበረው ልጅ ጋር ነው። አሏህ ይጠብቀን! አስብ ለኒካህ ሲፈልጋት፣ መድረሳ ውስጥ ነበረች፣ ዲን ላይ ጠንካራ ናት ብሎ ነው ያገባት። ልቧ ያለው ግን ያ በሀራም ሲደበርባት የነበረው ልጅ ጋር ነው። ያማል!!!
ጭራሽ አንዳንዶቹ ከመጀመሪያው ጋር በሀራም የጦፈ ወሬ ስለ ሚጀምሩ ጭራሽ ለኒካህ ቆርጦ የመጣውንም ይመልሳሉ።
ውስጣችን በወንጀል ያደፈ ሆኖ፤ ከላይ መልካም መስለን ብንታይም ሁሉን አዋቂ ከሆነው አሏህ ሚሰወር ነገር የለም! ሸሪዓችን ለሁሉም ነገር ልክ አስቀምጧል። ከልኩ ካለፍን ክሳራው በዱንያም በአኼራም ይጎዳናልና እንጠንቀቅ።
✍ ከ تراب መልእክት በትንሹ ኤዲት የተደረገ።
https://www.tgoop.com/tdarna_islam
BY ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
Share with your friend now:
tgoop.com/tdarna_islam/4563