tgoop.com/tdarna_islam/4951
Create:
Last Update:
Last Update:
አይ እኔና ስደት..................!!
አይ እኔና ሰደት ተስማምተን ያለነው!
አንዳፍታ አኩርፌ መልሸ እምወደው፡
ጠልቸ የማልጠላው ወድጀ የማልወደው፡
ስደት መምህሬ አንተን ብቻ እኮ ነው፡
ናፍቆቴ ሲጠና ክፍት ያለኝ ለታ፡
አማርርሀለሁ ከጧት እስከ ማታ፡
ደግሞ ልጠላህ አልችልም አለብኝ ውለታ፡
መምህሬ ሁነህ ብዙ አስተምረኸኝ፡
ከድቅድቅ ጨለማ ለመውጣት ስበቤ የሆንከኝ ፡
ስለ ድነል ኢስላም ብዙ ያሳውቀኸኝ፡
ድሮማ ነበርኩኝ መንገድ የጠፋብኝ፡
አንተ ነህ ስበቤ ሁሉን የመራኸኝ፡
ልጠላህ አልችልም ውለታህ አለብኝ፡
አንዳፍታ ብጠላህ ሲራ ሲበዛብኝ ፡
ውለታህን ሳስብ ተመልሸ ያውነኝ፡
ግን እንስማማለን አንድ ቀን አምናለሁ ፡
ተስፋየ በአላህ እጅ መሆኑን አውቃለሁ፡
አንድ ቀን አይቀርም ሀገር እገባለሁ፡
በሀያት ከቆየው እስከዛ ካለሁኝ፡
አጀሌ መቶ ሞትም ካልቀደመኝ፡
ከስደት ስመለስ ስላንተ አወራለሁ፡
በቃ ያን ቀን ነው እኔና አንተ የምንስማማ፡
ስደት እኔና አንተ እስከዛ እንቻለው።
➛ትድረስ ለሰሰደተኞች!!
=https://www.tgoop.com/tdarna_islam
BY ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
Share with your friend now:
tgoop.com/tdarna_islam/4951