tgoop.com/tikvahethiopia/93016
Last Update:
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ሄደዋል።
ትላንት አዲስ አበባ ከገቡ በኃላ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ የቀይ ባህር ጉዳይ ተነስቷል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ የመሆን ፍላጎቷ ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል።
ውይይቱን ተከትሎ መሪዎቹ የጋራ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመው (ዶ/ር) ፤ " ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን አክሰስ የማድረግ ፍላጎቷን በዝርዝር ተወያይተናል " ብለዋል።
" ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳነሳነው 130 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሀገር ፣ ኢኮኖሚዋ በፍጥነት እያደገ ያለ ሀገር ፣ ተጨማሪ የባህር በር አክስሰ የሚያስፈልጋት ሀገር በዓለም ህግ በሰላማዊ መንገድ ፣ በዴፕሎማሲያዊ መንገድ እንደ ፈረንሳይ ያሉ ወዳጅ ሀገራትን ተጠቅመን የምናገኝበት (የባህር ባር አክሰስ) መንገድ ላይ የእሳቸው ጠንካራ ድጋፍ እንዳይለየን የቀረበላቸውን ጥያቄ እሳቸውም በአክብሮት ተቀብለዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ፕሬዜዳንቱ የቀረበላቸውን ጥያቄ በመቀበላቸው ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት ከፈረንሳይ እና ከፕሬዜዳንት ማክሮን የሚጨበጥ ውጤት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦
➡️ በቅርቡ ኢትዮጵያ ያካሄደችውን ኢኮኖሚክ ሪፎርም ፈረንሳይ እና ቻይና ኮቼኤር የሚያደርጉት እንደሆነ ፕሮግራሙ እንዲሳካ ማክሮን ከፍተኛ ድጋፍ ለኢትዮጵያና ለሪፎርሙ እንዳዳረጉ ፤ የፈረንሳይ መንግሥት በቀጥታ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በEU እና IMF አይተኬ ድጋፍ እንዳደረገ ገልጸዋል።
➡️ ፈረንሳይ በኢትዮጵያ አንከር ኢንቬስተር ሆና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትን በማስተባበር በወሳኝ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን አሳውቀዋል።
➡️ " ማክሮን የሚገቡትን ቃል በመፈጸም የሚታወቁ ናቸው ፤ በኢንቨስትመንት ረገድም አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል " ብለዋል።
ፕሬዜዳንት ማክሮን ምን አሉ ?
ለኢትዮጵያ የባህር በር አክሰስ መኖር ላይ የተነሳው ጥያቄ ትክክለኛ እንደሆነ ማክሮን ገልጸዋል።
" ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የገለጹት የባህር በር መኖር አስፈላጊነት ፤ ለወደፊት ያሉትን ነገሮች ማመቻቸት መቻል ትክክለኛ ጥያቄ ነው " ያሉት ማክሮን " በዚህ ላይ ፈረንሳይ ባላት አቅም ልትጫወት የምትችለውን ሚና መወጣት ትፈልጋለች። ይሄ በምን አይነት መንገድ መሆን አለበት የሚለው በንግግር፣ በውይይት፣ ዓለም አቀፍ ህጎችን ባከበረ መልኩና ጎረቤት ሀገሮችን ባከበረ መልኩ መሰራት የሚችልበትን መንገድ ለኢትዮጵያና ለቀጠናው መሳካት እንዲችል ሚናችንን እንወጣለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዜዳንት ማክሮን ፦
👉 " ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ ተነጋግረናል ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም ማስፈን ይቻል ዘንድ ትልቅ እርምጃ መሆኑንና ለማሳካትም እየተሞከረ መሆኑን እንገነዘባለን ፈረንሳይ ከዚህ ጋር በተያያዘ ያሉ ነገሮችን ለመደገፍ ትፈልጋለች ፤ እርሻን ማበረታታ፣ የተጎዱ ሆስፒታሎችን መልሶ ማቋቋም ፤ ከሽግግር ፍትህ ጋር በተያያዘ ደግሞ የሚሰራውን ስራ የህግ የበላይነት የሚከበርበትን መንገድ ማየት እንፈልጋለን ለዚህ እናተ በምትጠይቁን መሰረት ከጎናችሁ ሆነን ሁል ጊዜ እንቀጥላለን " ብለዋል።
👉 " ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያመሰገንጉበት ጉዳይ በቱርክ ከሶማሊያው ፕሬዜዳንት ጋር የሰላም ንግግር መደረግ መቻሉን ነው ይሄ የሚደገፍ ነገር ነው። የሁሉንም ሉዓላዊነት ማክበር ጋር የሚያያዝ ነው። ከዛ በኃላ ግን ስለ ባህር በር መኖር አስፈላጊነት ጠቅላይ ሚኒስትር የገለጹ ትክክለኛ ጥያቄ ነው ፤ ፈረንሳይ ባላት አቅም ልትጫወት የምትችለውን ሚና ታመቻቻለች። በንግግር ፣ በውይይት ፣ ዓለም አቀፍ ህግ ባከበረና ጎረቤት ሀገሮች ባከበረ መልኩ " ሲሉ ገልጸዋል።
👉 " ከኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ ተነጋግረናል። በ2019 በመጣሁበት ጊዜ ያንን ታላቅ የኢኮኖሚ ሪፎርም ከመንግሥቶት ጋር በተያያዘ 100 ሚሊዮን ዩሮ በAFD አማካኝነት እንዲሁም የተለያዩ ቴክኒካል ድጋፎችንም መጨመር ችለናል። በአሁን ጊዜ ደግሞ ያለንን ሁሉ ነገር እንደምናደስ ለዚህም በ25 ሚሊዮን ዩሮ በጀት ድጋፍ ለማድረግ ነው። " ሲሉ ተናግረዋል።
👉 " ከኤሌክትሪክ ኔትዎርክ ጋር በተያያዘ የፈረንሳይ ድርጅቶች መግባት የሚችሉበት አጋጣሚ ይኖራል በዚህ ከአውሮፓ ህብረት ፈንድ ጋር እንዲሁም አውሮፓ ካሉ ባንኮች ጋር በመሆን 80 ሚሊዮን ዩሮ ይቀርባል " ብለዋል።
👉 " ከዕዳ ጋር በተያያዘ ከG20 ጋር የሚያያዘውን ከቻይና ጋር የሚሰራ ስራ ይኖራል። ይህ ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚቀርብ ነው። ባለፈው ፓሪስ ባዘጋጀነው ዝግጅት ተጨባጭ ነገር ተገኝቷል። ይህም እርሶ እያደረጉት ባሉት የሪፎርም ስራ ሲሆን 3 ቢሊዮን ዩሮ የምናመቻች ይሆናል እናተንም በሙሉ መደገፍ እንፈልጋለን ፤ መመቻቸት ስላሉባቸው ጉዳዮች ከIMF ጋር እንነጋገራለን " ብለዋል።
👉 " የፈረንሳይ ድርጅቶች ይበልጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ (በኢንቨስትመንት) ፍላጎት አለን " ሲሉ ገልጸዋል።
ማክሮን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ሀገራቸው ትልቁን ድጋፍ አድርጋበታለች የተባለውን የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ስራን ተመልክተዋል።
ፈረንሳይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ስራዎችን በግንባር ቀደምትነት በፋይናንስና ቴክኒክ ረገድ እየደገፈች ሲሆን ስራው 50% መሰራት እንደተቻለ ተነገሯል።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለፈረንሳይ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia