Telegram Web
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ 🔴 “ደስ ካላቸው በቀን ሁለት ጊዜ ካልሆነ አንድ ጊዜ ነው ምግብ የሚሰጡን። ምግብ ባጋጣሚ ስናገኝ ነው የምንመገበው” - ኢትዮጵያውያን በማይናማር ➡️ “ ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ‘የጎሳ ጦርነት አለ (ማይናማር)። ልጆቹን አስገድደው ወደ ጦርነት እንዳይከቷቸው ስጋት አለኝ’ ብሏል” - የወላጆች ኮሚቴ ወደ 600 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከእገታው ቦታ ወጥተው አስቸጋሪውን ስራ…
🚨 #Alert

“ ባለንባቸው ካምፓች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ህንፃው ተሰነጣጥቋል። ካጠገባችን የተደረመሰም አለ” - ከ730 በላይ ኢትዮጵያውን በማይናማር

በማይናማር ከ730 በላይ ኢትዮጵያውያን ባሉባቸው የተለያዩ ካምፓች 7.7 የተመመዘገበ መሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ለሞት እሩብ ጉዳይ ላይ ነን። ህንፃዎቹ ተሰነጣጥቀዋል። ከኛ አጠገብ የተደረመሰም አለ። እዚህ ባለመውጣታችን ስቃያችን በዝቷል። እባካችሁ አስወጡን” ሲሉ በሀዘን ስሜት ተማጽነዋል።

BGF ካምፕ በሦስት ህንጻዎች በተከታይ 204፣ 118፣ 59 በድምሩ 381፤ KK2 PARK አካባቢ 62፣ KK4 PARK አካባቢ 37፤ በአጠቃላይ ቢዲኤፍ ካምፕ 480፣ DKBA ካምፕ 255 ኢትዮጵያውያን እንዳሉ፤ በነዚሁ በሁሉም ህንፃዎች መሬት መንቀጥቀጡ እንደተከሰተ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ?

“ዛሬ ኢትዮጵያውያን ባለንባቸው ህንጻዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። እኛ ለጊዜው ተርፈናል፤ የተጎዳም የለም።

ያለንበት ህንፃ ግን ተሰነጣጥቋል። የተደረመሰ ህንፃም አለ ካለንበት ትንሽ ራቅ ያለ። ከ40 በላይ የሥፍራው ሰራተኞች ተጎድተዋል።

ኬቢጅኤፍ ካምፕ 480፣ ዲኬቢኤ 255 ኢትዮጵያውያን አለን። በፍጥነት ወደ ታይላንድ ብሎም ኢትዮጵያ አለመጓዛችን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እየዳረገን ነው።

ተደራራቢና ጽኑ ህመም የሚሰቃዩ፣ እንዳናጣቸው እያሰጉን ያሉ ልጆች አብረውን አሉ። የጦርነቱም ድምጽ ከእለት እለት ወዳለንበት አካባቢ እየተጠጋ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻርተር ፕሌን ልኮም ቢሆን በቶሎ የምንወጣበትን ሁኔታ ካልተፈጠረ አስቸጋሪ ነው። አሁን ላይ ስጋት፣ ድብርት፣ ጭንቀት ጽኑ ህመም፣ የብዙዎቻችን ፈተና ሆኗል።

ቢዲኤፍ ካምፕ ላይ 260 ኢትዮጵያውያን አለን። የመሬት መንቀጥቀጡ እኛም ጋ ተከስቷል። ዶርም ውስጥ ነበርን ውጭ ወጣን ሲከሰት። 

እግዚአብሔር ይመስገን በዛሬው መሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት አልደርሰብን። ለቀጣዩ ግን ከሌላው ስቃያችን በተጨማሪ ይህን ከፍተኛ ስጋት ደቅኖብናል።

መንግስት ምነው እንደዚህ እከምሆን ዝም አለን?” ሲሉ ጠይቀዋል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ (USGS) በማይናማር የተከሰተውን መሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 7.7 የመዘገበው ሲሆን፣ የቻይናው የመሬት መንቀጥቀጥ ኔትወርክ (CENC) ደግሞ በሬክተር ስኬል 7.9 የተመዘገበ መሆኑን አሳውቋል።

(ቪድዮ እና ፎቶ፦ ባንኮክ እና ማይናማር)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Amahra : የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግስቴ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

ዛሬ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አረጋ ከበደ የተለያዩ ሹመቶችን መስጠታቸው ተዘግቧል።

በዚህም ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ሲያገለግሉ የቆዩትን ኮሚሸነር ዘላለም መንግስቴ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አደርገው ሾመዋቸዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም አቶ አስቻለ አላምሬ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አድርገው ሾመዋል።

@tikvahethiopia
" የስነ ምግባር ግድፈቶች ተብለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል " - ካውንስሉ

➡️ " የበሻሻው ዐቢይ እና የሾለው ነብይ በተራ ጫጫታ ይጠፋሉ ብሎ ማሰብ ተራ ቅዠት ነው  " - ነቢይ ኢዩ ጩፋ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በነብይ ኢዩ ጩፋ የሚመራውን የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ማገዱን ይፋ አድርጓል።

በካውንስሉ የጽ/ቤት ሃላፊ ፓስተር ጌትነት ለማ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ የቤተክርስቲያኒቱን መታገድ ያረጋግጣል።

በካውንስሉ የምዝገባ ቁጥር 03111 በሃይማኖት ተቋምነት አባልነት የተመዘገበችው የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ሊታገድ እንደሚችል ካውንስሉ ከሁለት ቀን በፊት በሰጠው መግለጫ ጥቆማ ሰጥቶ ነበር።

ካውንስሉ " ቤተክርስቲያኒቱ የካውንስሉ አባል ስትሆን ልታከናውናቸው ከሚገቡ መመሪያዎችና ደንቦች መካከል አንዱ የካውንስሉ አባላት ስነ ምግባር መመሪያ ሲሆን በስነ ምግባር መመሪያው አንቀጽ 9.3 ላይ የስነ ምግባር ግድፈቶች ተብለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል " ብሏል።

እግዱም በካውንስሉ ሥነ መለኮት ኮሚሽን እና የሕግ ኮሚሽን ታይቶ በሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጡበት ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ታግዳ እንደምትቆይ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከቀናት በፊት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በወቅቱ መግለጫውን የሰጡት የካውንስሉ የጽ/ቤት ሃላፊ ፓስተር ጌትነት ለማ " ዘይት መሸጥ እንደማይችሉ ከዚህ ቀደም ነግረናል አሁን ዘይት እየሸጡ ያሉ ተቋማት እና ግለሰቦች ዝርዝር መረጃዎች ተጠናቅሮ ደርሶናል በዚህ መሰረት በቅርቡ ተወስኖ ለሚዲያ ይፋ ይደረጋል ደንባችን ላይ በተቀመጠው መሰረት የሚገባውን ውሳኔ እናስተላልፋለን " ብለው ነበር።

የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች መሪ ነብይ ኢዩ ጩፋ መጋቢት 11 ወደ ሃዋሳ ከተማ ሲገቡ የታየውን ትእይንት አስመልክቶ የተናገሩት ፓ/ር ጌትነት " በጦር መሳሪያ ታጅቦ ወደ ከተማ የሚገባበት ሁኔታ የወንጌል አማኞችን አስተምህሮ በፍጹም የሚቃወም ነው እንቃወመዋለን " ብለው ነበር።

በዝርዝር ባነሱት ሃሳብ ምን ብለው ነበር ?

" የመንግስት አካላት አንድ አገልጋይ ወደ ከተማ ሲገባ ፖሊስ አሰልፈው፣ መሳሪያ አስታጥቀው፣ አጀብ ፈጥረው ግርግር በማድረግ ከተማው ላይ ሌላ አካል የገባ እስኪመስል ድረስ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን አናምንም።

ይህን ማድረጋቸው ለወንጌል አማኞች ክብር መስጠትም አይደለም የመቃብር ስፍራ አጥቶ የሚቸገር የወንጌል አማኝ ስላለ የመንግስት አካላት እሱን ያድርጉልን።

በተደጋጋሚ እንደዚህ የሚያደርጉ የተለያዩ ስያሜ ያላቸው አገልጋዮች ሊታረሙ ይገባል ብለን በጥብቅ ነው የምንቃወመው ፈጽሞ የወንጌል አማኞች ኢሜጅም አይደለም ።

በመሳሪያ ታጅቦ በዛ ሁሉ ግርግር ወደ አንድ ከተማ መግባት ምንድነው ትርጉሙ ...ለእኛ ትርጉም አልባ ነው።

እንደዚህ አይነት ነገሮችን አስመልክቶ በቅርቡ መግለጫ እንሰጣለን መታገድ ያለባቸው ካሉም ይታገዳሉ በፍጹም ኮምፕሮማይዝ አናደርግም ምክንያቱም በካውንስሉ አብረን ስናመልክ ካውንስሉ ለእንደዚህ አይነት ነገሮች ጥላ ሆኖ አይደለም።

እንዲታረሙ፣ እንዲመለሱ ፣ እንዲስተካከሉ በተደጋጋሚ በፅሁፍ፣ በአካል ተነግሯቸዋል ሰርተፍኬት ሲወስዱ ፈርመዋል ይሄ ሁሉ ተደርጎ ' አንመለስም ' ብለው የዘይት ንግዳቸውን ከቀጠሉበት ዘይት መነገድ በካውንስሉ ፈቃድ ፈጽሞ አይቻልም።

ለሁሉም ክልሎች ይፋዊ ደብዳቤ ጽፈናል ቢጠየቁም እንኳን የመንግስት አካላት እንደዚህ አይነት መሳሪያ ይዞ ማጀብ ተገቢ አይደለም። " ነበር ያሉት።

የካውንስሉን መግለጫ ተከትሎ ነቢይ እዩ ጩፋ በትላንትናው ዕለት በድምጽ መልእክት ሃሳባቸውን ሰጥተው ነበር።

በዚህም " የክርስቶስ አምባሳደር ወደ ከተማ ይመጣል ተብሎ ማርሽ ባንድ ብቻ አይደለም ካላንደር ሊዘጋ ይችላል ፤ ገና መድፍ ይተኮሳል " ሲሉ ተደምጠዋል።

ነቢይ እዩ ጩፋ በዝርዝር ምን አሉ ?

" በመጀመሪያ የመንግስት ፓትሮል የሚወጣው ዌልካም ለማለት የሚወጣውን የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ነው ይህ የመንግስት ተቀዳሚ ሃላፊነት ነው በመቀጠል አምላክ የላከው አገልጋይ ወደ ከተማ ሲገባ ዌልካም ለማለት ነው የሚወጣው።

ከዚህ በኋላ ቪ8 ቶች (መኪኖች) ቪ8 ቶች ብቻ አይደለም በዚህ ዘመን የተፈጠረም ነገር ካለ ተጨምሮ አገልጋዮች ዌልካም ይባላሉ።

ለመቀበል እንደምትቸገሩ አውቃለሁ ነገር ግን ምርጫ የላችሁም አገልጋዮችን በንቀት አትዩ።

አገልጋዮች የእግዚአብሔር ድምጽ ፣ቃል አቀባዮች እና ምልክቶች ናቸው።

በማስፈራራት እና በማስጨነቅ ቀጥሎ የሚነሳውን ትውልድ ተስፋ ለማስቆረጥ የምትፈልጉ ሰዎች እኔ አለሁ ከዚህም በኋላ ፊት ለፊት ቆሜ ለሚመጣው ትውልድ በር ለመክፈት ከፊት አለሁ።

አንዳንድ ሰዎች ዘመኑ በሚመጥን መልኩ መንቀሳቀስን እንደ ሃጥያት ያያሉ።

ሰባት እና ስምንት ፓትሮል ለምን ይመደባል ? በዚህ ልክ መታጀቡ ለምን አስፈለገ ? የምትሉ ሰዎች ለአገልጋዮች መንግስታዊ የሆነ ጥበቃ ፣ ከለላ፣ ዌልካም ያስፈልጋል።

አንድ በእግዚአብሔር ለተሾመ አገልጋይ ምን ያህል ክብር እንደሚገባ መንግስት እና መንግስታዊ የሆኑ መዋቅሮች በተረዱበት በዚህ ጊዜ የቤተክርስቲያን መሪዎች አይናቸው መከደኑ ከምንም በላይ የሚያስገርም ነው።

ቪ8 በዛ፣ ፓትሮል በዛ የምትሉ ሰዎች እግዚአብሔር ባንተ ኮልኮሌ እንዲታጀብ ነው የምትፈልገው ? እግዚአብሔር በፓትሮል የሚታጀብ አምላክ አይደለም ፓትሮሉም ለኛ ነው እኛ ነን የምንታጀበው ከዚህ በኃላ።

ብታምኑም ባታምኑም በኢትዮጵያ ምድር በራሳቸው ጀት እየተንቀሳቀሱ የሚያገለግሉ አደገኛ ሰዎች ይነሳሉ።

የምታስተላልፉት መልዕክት ተስፋ ከመቁረጥ የመነጨ ይመስላል።

ሀዋሳ ስንገባ የተደረገልን አቀባበል ያስደነገጣችሁ ሰዎች ሰላም ናችሁ ? ለማንኛውም ከዚህ በኃላ በሚደረጉ ክሩሴዶች ከዚህ የበለጠ ነገር እንደሚሆን እንዳትጠራጠሩ ከወዲሁ አረጋግጥላችኋለሁ።

የበሻሻው ዐቢይ እና የሾለው ነብይ በተራ ጫጫታ ይጠፋሉ ብሎ ማሰብ ተራ ቅዠት ነው " ብለዋል።


የካውንስሉን እግድ በሚመለከት እስካሁን ከቤተክርስቲያኒቱ የተሰጠ መግለጫ የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Thailand : በማይናማር አከባቢ በተከሰተው ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በታይላንድ ባንኮክ በመገንባት ላይ ያለ ህንጻ ተደርምሷል። በርካታ ሰራተኞች ህንጻው ሳይደረመስባቸው እንዳልቀረ ተነግሯል። በባንኮክ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። Video - Social Media #Myanmar  #Earthquake #Bangkok Via @Tikvahethmagazine
#Maynamar : ማይናማር ባጋጠማት ከባድ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን 144 ዜጎቿ ህይወት ጠፍቷል።

732 የሚሆኑት ተጎድተዋል።

ታይላንድ ባንኮክ ደግሞ እስካሁን በታወቀው 3 ሰዎች ሞተዋል።

ማይናማር ሬክተር ስኬል 7.7 በሆነ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው የተመታችው።

@Tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

አባት ህይወቱ አልፏል።

በመቐለ በቤት የተቀመጠ ቤንዚን ባባሰው የእሳት ቃጠሎ የተጎዱ ቤተሰቦቹን ለማዳን ጥረት አድርጎ ሳይሳካለት ቀርቶ ከባድ ጉዳት ደርሶት ሆስፒታል ገብቶ በጤና ባለሙያዎች ክትትል ስር የነበረው አባት  መጋቢት 18/2017 ዓ.ም ህይወቱ አልፏል።

በአሰቃቂው አደጋ ምክንያት እናት ዕድሚያቸው 5 ወር እና 4 ዓመት ትኩል ከሆኑ ልጆቿ ጋር ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Maynamar : ማይናማር ባጋጠማት ከባድ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን 144 ዜጎቿ ህይወት ጠፍቷል። 732 የሚሆኑት ተጎድተዋል። ታይላንድ ባንኮክ ደግሞ እስካሁን በታወቀው 3 ሰዎች ሞተዋል። ማይናማር ሬክተር ስኬል 7.7 በሆነ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው የተመታችው። @Tikvahethmagazine
#Update

“ ካለንበት ህንጻ እንዳንወጣ ሚሊተሪዎች በሩን ዘግተው ከልክለውናል ” - ኢትዮጵያውያን በማይናማር

በማይናማር በከፋ ስቃይ ከሚገኙ ዜጎች መካከል በመሬት መንቀጥቀጡ አንድ ኢትዮጵያዊ ጉዳት እንደደረሰበት ኢትዮጵያውያኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያኑ በሰጡን ቃል ምን አሉ ?

“ ኢትዮጵያዊያን በምንገኝበት ቀጠና የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ሊከሰት እንደሚችል የማስጠንቀቂያ መረጃዎች እየወጡ በመሆናቸው ከፍተኛ ስጋት ላይ ነን። 

ካለንበት ህንጻ እንዳንወጣ ደግሞ ሚሊተሪዎች በሩን ዘግተው ከልክለውናል።

ቀን ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ KK 4 ካምፕ  የነበረ ወንድማችን በአደጋው ድንጋጤ በጥድፊያ ከፎቅ ለመውረድ ሲሞክር እግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበታል።

እንደተተነበዬው ሆኖ ችግሩ ከተከሰተ ከፍተኛ ጉዳት ይደርስብናል የሚል ስጋት አለን። አሁን የሌሊት ቢሆንም በስጋት ለመተኛት የደፈረ የለም።

ብዙ ኢትዮጵያውያን በስጋት ከቤት ውጪ (ከግቢ ውስጥ) ነው ያለነው። በሀገሪቱ ኃላፊዎች ‘መሬት መንቀጥቀጡ በ24 ሰዓት ውስጥ ድጋሚ ሊከሰት ይችላል’ የሚል ማስጠንቀቂያ እየተላለፈ ነው።

ያለንባቸው ህንፃዎች ፊንሺንግ ላይ ያሉ ናቸው። የቆዬው ህንፃም ቢሆን በአደጋው ሊጎዳ ይችላል ግን አዲስ እየተሰራ ያለው ህንፃ ያለው ደግሞ ጉዳቱ ሊብስበት ይችላል።

በዛሬው አደጋ ኮሎናቸው የፈራረሱ ያለንባቸውጨህንፃዎች አሉ። የኢትዮጵያ መንግስትን ይሁንታ ነው የሚጠብቀውና ቶሎ እንዲያስወጣን በአክብሮት እንጠይቃለን ” ብለዋል።

ዛሬ በባንኮክና ማይናማር በተከተው 7.7 ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከ150 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መጎዳታቸው ተነግሯል።

በማይናማር በተለያዩ ካምፓች የሚገኙ ከ735 በላይ ኢትዮጵያውያንም የድረሱልን ተማጽኖ እያሰሙ ይገኛሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Ramadan

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሀጅ ተጓዦችን የሚያስተናግዱት አል-ሀራም መስጂድ / በመካ የሚገኝ ትልቅ መስጂድ / እና በመዲና የሚገኘው መስጂድ አን ናባዊ / የነብዩ መስጂድ / በፎቶ።

በእስልምና ውስጥ እጅግ የተቀደሱ ቦታዎች ናቸው።

በዓለማችን የሚገኙ ግዙፍ መስጂዶችም ናቸው።

በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩና ከዓለማችን የተለያዩ ክፍሎች የሚመጡ ሙስሊሞች ለእስላማዊ ሃይማኖታዊ ስርዓት ሀጅ በእነዚህ የተቀደሱ ስፍራዎች ይገኛሉ።

#Islam #Ramadan #AlMasjidanNabawi #MasjidalHaram

Photo Credit - Haramain (2025)

@tikvahethiopia
2025/03/29 00:00:34
Back to Top
HTML Embed Code: