TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የትግራይን ህዝብ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል" - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ " ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች መልእክት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለዋል።
ሰልፉን የጠራው የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያዘጋጀው መልእክት የተቀበሉት ፕሬዜዳንቱ አቶ ጌታቸው ፥" ከጦርነት ወጥተን በተነፃፃሪ ሰላም በምንገኝበት ጊዜ ሴት ሙስሊም እህቶቻችን በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ሲከለከሉ ማየት በጣም የሚያሳዝን ነው " ብለዋል።
" ችግሩ ገና ከጅምሩ ከትምህርት ቤቶቹ አመራሮች ፣ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ በመነጋገር ለመፍታት ጥረት ሲደረግ ቆይተዋል። እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ያልነበረት ጉዳይ ነው። አሁንም የትግራይ ህዝብ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲፈታ ይደረጋል " ብለዋል።
" ጉዳዩ ቶሎ መታረም እንዳለበት የሚያግባባን ቢሆንም ፤ ከስሜት በፀዳ አስተዋይነትና ዘላቂነት ባለው መንገድ መሆን እንደሚገባ ሁላችንም መገንዘብ ያስፈልጋል " በማለት አክለዋል።
ችግሩ በፍጥነት እንዲፈታ አስተዳደራቸው ዝግጁ እንደሆነና እንደሚሳራም አመልክተዋል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የተነሳ ጥያቄ አጀንዳ መሆን አልነበረበትም ብሎ እንደሚያምን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተባባሪዎቹ እና ተሳታፊዎቹ ላሳዩት ጭዋ የሆነ ባህሪ ምስጋና አቅርበዋል።
ሰላማዊ ሰልፉ ፍፁም ሰላም በሆነ መንገድ መጠናቀቁን ሰልፉን በቦታው ሆኖ ሲከታተል የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
@tikvahethiopia

tgoop.com/tikvahethiopia/93944
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA
Share with your friend now:
tgoop.com/tikvahethiopia/93944