በዐድዋ ድል የቤተክርስቲያን ሚና
መ/ር ጌታቸው በቀለ
✍️ዐፄ ምኒልክ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
ስዕለት ተሥለዋል፡፡
✍️ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስና ዕጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ በመላ ሀገሪቱ ጸሎት፣
ኀዘንና ምህላ ዐውጀው ነበር።
✍️ ከዘመቻው በፊት ዘማች አብያተክርስቲያናትም ተለይተዋል፣
✍️ በዘመቻውም ታቦት፣መስቀል፣ ንዋያተ ቅድሳት ጥላዎች እና
ድባቦች ይዘው ሊቃውንቱ እና ካህናት ዘምተዋል።
የዐድዋ ጦርነት የካቲት 23 ቀን በዕለተ ሰንበት በ6 ሰዓት ውስጥ በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት፣ በጀግኖች አባቶቻችን አርበኝነት ተጋድሎ በኢትዮጵያ የበላይነትና ድል አድራጊነት ተጠናቀቀ፡፡
ይህንንም ድል በየዓመቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ ታከብረዋለች፡፡ ዘንድሮም ለ129ኛ ዓመት ይከበራል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡ በዐድዋው ድል የቤተክርስቲያንን አስተዋጽኦ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን ተራዳኢነት በስፋት ታስተምራለች፡፡ ታሪኩን እንደሚከተለው እንመለከታለን፡-
የዐድዋን ድል
የዐድዋ ድል ለዘመናት ተከብሮ የኖረውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ሀገርነትና ነፃነትን ከማረጋገጡም በላይ ለሀገራችን ዓለም አቀፍ ዝናን አጐናጽፏታል፡፡ የዐድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን የትብብር፣ የአንድነት፣ የኩራትና የክብር ምንጭ ከመሆኑ ባሻገር፤ የድሉ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ለጥቁሮች ነፃነትና የክብር ፋና ለመሆን በቅታለች፡፡ የዐድዋ ድል ምሳሌነት አፍሪካውያን በቅኝ ገዥዎቻቸው ላይ አንዲነሡ ምክንያት ሆኗል፣ ለፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ መፋፋምም ጉልህ አስተዋጽኦ አበርከቷል፡፡ ከዚህ አልፎ የዐድዋ ድል ከነጮች ተጽዕኖ ነፃ የሆነ የጥቁሮች የሃይማኖት እንቅስቃሴ እንዲጀመር ምክንያት እስከ መሆን ደርሷል፡፡ ለአብነትም ኢትዮጵያኒዝም እየተባለ ይጠራ የነበረውና በተለይ በአሜሪካና በደቡብ አፍሪካ የነበረውን እንቅስቃሴ መጥቀስ ይቻላል፡፡
በዐድዋ ድል የቤተክርስቲያን ሚና
ለዐድዋ ድል መገኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሚና እጅግ የላቀ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ይህች ጥንታዊ ቤተክርስቲያን በዐድዋ ጦርነት ወቅት ከመነሻው እስከ መጨረሻው፣ ከዘመቻው እስከ ድሉ፣ ከዋዜማው እስከ ጦርነቱ በመሪነትና በተሳታፊነት ነበረች፡፡ ቤተክርስቲያኗ ሕዝቡን በመቀስቀስ፣ አመራር በመስጠት፣ አብራ በመዝመት፣ የሥነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖር በማድረግ፣ በጦርነቱ በመሳተፍ፣ መረጃ በመስጠትና በማስቀመጥ ባደረገችው አስተዋጽዖ ተወዳዳሪ አልነበራትም፡፡ በዐድዋ ጦርነት ወቅት ቤተክርስቲያኗ የነበራትን የላቀ ሚና ለመረዳት የዐፄ ምኒልክን የክተት ዐዋጅ መመልከት በቂ ነው፡፡ ዐዋጁ ጦርነቱ ከቤተክርስቲያን፣ ከእግዚአብሔር እና ከወላዲት አምላክ ጠላት ጋር እንደሆነና የመጣው ጠላት አገር የሚያፈርስ ብቻ ሳይሆን፤ ሃይማኖት የሚለውጥ ጭምር መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ዐዋጁ እንደሚከተለው ነበር፡-
ስማ፣ ስማ፣ተሰማ የማይሰማ የእግዚአብሔር እና የወላዲት አምላክ ጠላት ነው፡፡ ስማ፣ ስማ ተሰማማ፣ የማይሰማ የእግዚአብሔርና የቤተክርስቲያን ጠላት ነው፡፡ ስማ፣ ስማ ተሰማማ፣ የማይሰማ የእግዚአብሔርን የንጉሡ ጠላት ነው፡፡ እግዚአብሔር ወሰን እንዲሆን የሰጠንን ባሕር አልፎ ሃይማኖት የሚለውጥና ሀገር የሚያጠፋ ጠላት መጥቶአል፡፡ እኔ ምኒልክ በእግዚአብሔር ርዳታ ሀገሬን ለጠላት አሳልፌ አልሰጥም፡፡ ያገሬ ሰው! ከአሁን ቀደመ የበደልኩህ አይመስለኝም፡፡ አንተም እስካሁን አላስቀየምኸኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ርዳኝ፣ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለሚስትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በኅዘን ርዳኝ፡፡ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፣ አልተውልህም፡፡ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም፡፡ ዘመቻዬም በጥቅምት ነው፡፡
ዐፄ ምኒልክ ዐዋጅን ካስነገሩ በኋላ በአዲስ አበባ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸሎት ማድረሳቸውና ስእለት መሳላቸው የጦርነቱ መንፈሳዊ ዝግጅት አካልና ለቤተክርስቲያኗ ልዩ መልእክት የነበረው ነው፡፡ ስእለታቸውም “አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሉን ቢሰጠኝ ይህን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሣር ክዳኑን ለውጬ ባማረ ሕንፃ አሠራዋለሁ ” የሚል ነበር፡፡ ይህንም ስእለታቸውን ከድል በኋላ ፈጽመውታል፡፡
የክተት ዐዋጁን ተከትሎም በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስና በዕጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ በመላ ሀገሪቱ ጸሎት፣ ኀዘንና ምህላ ታወጀ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቤተክርስቲያን አስተምህሮው ተጠናከሮ ቀጠለ፡፡ አገር ከሌለ ሃይማኖት የለም፣ ሃይማኖትና ነፃነትን ማጣት ሽንፈት ነው፣ ወደ ፈጣሪ ለአገርና ለሃይማኖት ታግሎ መሔድ ሰማዕትነት ነው፣ ኢትዮጵያን ያህል አገር ማጣት እግዚአብሔርን ከሚያህል ጌታ መለየት ሞት ነው፣ ስለ አገር፣ ሃይማኖትና ነጻነት መሞት ክብር ነው ወዘተ… የሚሉት ርእሰ ጉዳዮች አንኳር ጉዳዮች ነበሩ፡፡ ከዚያም በቤተክርስቲያን

👍4
የአዝማች ኮሚቴ ተቋቋመ፣ ዘማች አብያተ ክርስቲያናትም ተለይተው ታወቁ፡፡ በዘመቻውም ታቦት፣መስቀል፣ ንዋያተ ቅድሳት ቃጭል፣ጥላዎች እና ድባቦች ይዘው ከሊቃውንቱና ካህናቱ ጋር እንዲዘምቱ ተወሰነ፡፡
ከአዲስ አበባ እስከ ዐድዋ በነበረው የዘመቻ ጉዞ ቤተክርስቲያኗ ግምባር ቀደም ሆና ሕዝቡን ከጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ጋር በአንድነት በመምራት የዘማቹን ወኔ በመገንባት፣ ስለ አገር ፍቅር በመሰበክ፣ በጾምና በጸሎት ወደፊት ትገሰግስ ነበር፡፡ በጉዞው ወቅት በሊቀ ጳጳሱ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስና በዕጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ አስተባባሪት መንፈሳዊ አገልግሎቱ በመዓልትና በሌሊት በሰዓታት፣ በማኅሌት፣ በቅዳሴ በነግህና በሠርክ ጸሎት ሳይቋረጥ ይከናወን ነበር፡፡ የጦር መሪዎቹ ሳይቀር በጸሎታቸው የተጉ የመንፈሳዊ ልዕልና ያላቸው ነበሩ፡፡ በየካቲት 14 ቀን 1888 ዓ.ም ዐፄ ምኒልክ ዐድዋ ሲደርሱ ከመላው ትግራይ የተውጣጡ ካህናትና ሊቃውንት ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በደማቅ ሁኔታ ተቀብለዋቸዋል፡፡ ከዚያም ለአንድ ሱባኤ ምህላ ታዟል፡፡ ዐፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ሱባኤ ይዘው የቆዩት በእንዳ አባ ገሪማ ገዳም ነበር፡፡ ለጦርነቱ ዝግጅትና መሰናዶ ሲጀመርም አስቀድሞ የታወጀው የጸሎትና የምህላ ዐዋጅ ነበር፡፡ ወደ ጦር ግንባር ሲዘምቱ ታቦታት፣ መስቀሎችና ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳት ተይዘው ነበር፡፡ የሃይማኖት አባቶችና የአብነት ተማሪዎች ሳይቀር በጦርነቱ ተሳትፈዋል፡፡ በመጨረሻም ለመላው ዘማች ለሰባት ቀናት የቁም ፍታት ተካሂዷል፡፡
በጦርነቱ ዋዜማ ዐፄ ምኒልክ፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ ራስ መኰንን፣ ራስ መንገሻ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ዐድዋ በሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስቀድሱ ነበር፣ ቅዳሴውም የተመራው በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ነበር፡፡ አቡነ ማቴዎስ “ልጆቼ ሆይ ዛሬ የእግዚአብሔር ፍርድ የሚፈጸምበት ቀን ነውና ሂዱ ለሃይማኖታችሁ ለአገራችሁ ሙቱ እግዚአብሔር ይፍታህ” ሲሉ መኳንንቱ ሁሉ እየተሽቀዳደሙ የአቡኑን መስቀል ተሳልመው ወደ ጦርነት መሄዳቸው፣ ሊቀ ጳጳሱም ወደ ጦርነት የሚገባውን ወታደር ሁሉ እግዚአብሔር ይፍታህ እያሉ ይናዝዙ እንደነበር ይነገራል፡፡ ዐፄ ምኒልክም በበኩላቸው ነጋሪት እያስጐሰሙ ሠራዊቱን “የጦርነት ድምፅ ብትሰሙም አትደንግጡ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ሆኖ ጠላቶቻችሁን ስለሚዋጋ አትፍሩ፣ እግዚአብሔር አምላካችሁ በፊታችሁ እየኼደ ጠላቶቻችሁን ስለሚዋጋላችሁ፣ እናንተንም ስለሚያድናችሁ ከፊታቸው አትሽሹ” በማለት ያበረታቱ ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላም አንጸባራቂው የዐድዋ ድል በየካቲት 23 ቀን በዕለተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተበሰረ፡፡
እንደ ማጠቃለያ
የዐድዋ ድል ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በነጻነት የግዛት አንድነቷ ተጠብቆ፣ ዳር ደንበሯ ተከብሮ ለዚህ ትውልድ እንድትደርስ በማድረግ በኩል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያደረገችው የላቀ፣ ዘመን ተሻጋሪና ዘርፈ በዙ አስተዋጽኦ አንዱና ዋነኛው ማሳያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አባቶችና እናቶች ታሪክና ቅርስን ብቻ ሳይሆን በከፈሉት መሥዋዕትነት ሀገርንም አቆይተውልናል፡፡ ይህ ትውልድ እንደ አባቶቹ ታሪክ መሥራት ባይችልም እንኳ ታሪኩንና ቅርሱን ማወቅና መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ የቤተክርስቲያንንም አስተዋጽኦና ውለታ መርሳት የለበትም፡፡ የዐድዋ ድል የኢትዮጵያዊ አንድነታችን ውጤት ነው፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት፣ በረከት፣ አማላጅነት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት
✍️ የኢትዮጵያ አንድነትና ኢጣልያ፡፡
✍️ አድዋና ምኒልክ
✍️ ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት፡፡
✍️ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ፡፡
✍️ ታሪክ ነገሥት ዘዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፡፡
✍️ Memories of the Victory of Adwa
✍️ The Life and Times of Menelik II of Ethiopia 1844-1913.
✍️ The Battle of Adowa

ግዕዝ በግዕዝ ትርጓሜ ወንጌል ዘ ምሁር ኢየሱስ ማቴ 11፥19 ደሞ እንዲህ ይላል...
እግዚአብሔር ቃል ሰው በሆነ ጊዜ እርሱ ለአዳም #ከኃጢአት_አስቀድሞ_የሆነውን_ሥጋ_እንደ_ተዋሐደ_ልታውቅ_ይገባል። ሕማመ ሥጋ፣ ኵነኔ በአዳም የተደረገችው አዳም የፈጣሪውን ትእዛዝ ባፈረሰ ጊዜ ነው። ነገር ግን #በተፈጥሮው_በባሕርዩ_እነዚህ_ገንዘብ_የሆኑት_አይደለም። ክርስቶስም ከነዚህ የወደደውን ይቀበል ነበር እንጂ። በዚህም ምክንያት ከነርሱ የተነሣ የሚፈተን አይደለም"

👍2❤1
ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
ግዕዝ በግዕዝ ትርጓሜ ወንጌል ዘ ምሁር ኢየሱስ ማቴ 11፥19 ደሞ እንዲህ ይላል... እግዚአብሔር ቃል ሰው በሆነ ጊዜ እርሱ ለአዳም #ከኃጢአት_አስቀድሞ_የሆነውን_ሥጋ_እንደ_ተዋሐደ_ልታውቅ_ይገባል። ሕማመ ሥጋ፣ ኵነኔ በአዳም የተደረገችው አዳም የፈጣሪውን ትእዛዝ ባፈረሰ ጊዜ ነው። ነገር ግን #በተፈጥሮው_በባሕርዩ_እነዚህ_ገንዘብ_የሆኑት_አይደለም። ክርስቶስም ከነዚህ የወደደውን ይቀበል ነበር እንጂ።…
አባቶቻችን በሥልጣን የሰበኩት ይኽ ነው።
ቅድስት ድንግል ማርያም ያልወደቀችው ሔዋን ናት።
ልክ አዳምና ሔዋን ሲፈጠሩ ንጹሓን ኾነው እንደተፈጠሩት።እንዳልወደቀው አዳም ንጽሕት ናት።
".....The key to understanding all these graces is Mary’s role as the New Eve, which the Fathers proclaimed so forcefully. Because she is the New Eve, she, like the New Adam, was born immaculate, just as the First Adam and Eve were created immaculate. Because she is the New Eve, she is the mother of the New Humanity just as the first Eve was the mother of humanity. And, because she is the New Eve, she shares the fate of the New Adam."
ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው እንደጻፉት

👍3
የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አንሁን ።
ይሄ የአበው ብሂል ነው። ምናልባትም አሁን በምድያው መልስ ሰጭ እና አጻፋዊ መልስ ሰጭ ሁነን ዱላ ቅብብሎሽ፤ ኳስ ውርዋሮሽ የመሰለ፥ ፍቅር የተለየው ፤ የተሰሚነት ስሜት እና የሊቅነት ስሌት የተጫነን ሰዎች አለን መሰለኝ? እንረጋጋ። እገሌ ወእገሌ አላልኩም። እገሌም እረፍ ።እነ እገሌም እረፉ። እነ እገሌም እንረፍ ያልኩት ። ይሄ የእውቀት እና የሊቅነት ቁመና የምንለካካበት አደባባይ አይመስኝለም።
✍️የጅብ ችኩሎች አንሁን። የጅብ ችኩል ስንት የሚበላ ሥጋ እያለለት ዘሎ ቀንድ ይነክሳል። እነ ልብ እነ ሳምባ፤ እነ ጉበት ፤ እነ ቆሽት እነ የጭን ሥጋ እያሉለት ዘሎ ቀንድ ይነክሳል። ቀንድ ደግሞ ስንኳን ሊበሉት እራሱ ይበላል።እበላለሁ ሲሉ መበላት አለ። ምናልባትም ቀንድ ቀንድ ነውና መብሊያህን ቀዶ ጥርስህን አውልቆ ምላስህን ቆርጦ መናገሪያም ማላመጫም ሊያሳጣህ ይችላል። ለዚህ መድኅኒቱ አለመቸኮል ነው ።
✍️ መቸኮልህ የማይነከስ ያስነክስሃል። ባትቸኩል ኑሮ ብዙ የሚነከስ ይቅርና የሚበላ ክፍል ነበረልህ። ከመቸኮልህ የተነሳ መቸኮልህ ወደ ቀንድ ላከችህ ። የቸኮለ ጅብ ይሄው ነው። ጅራት ይዤ ልከተል አይልም። በጉያ ወይም በውስጥ ገብቼ ብዙ ነገር ላግኝ አይልም። ዘሎ ቀንዷን ነው። ይሄ ድርጅቱ ደግሞ አስዉግቶት ያርፋል። መወጋት ደግሞ ከባድ ኑው። ያው በትልቅ ቀንድ መዋጋት ከባድ ነው። ነገረ ድኅነት እናስተምር ስንል እንዳንድን ሁነን እንዳንወጋ ብየ ነው ። ችኩል ግን ለምን ወደ ቀንድ እንደሚሮጥ አላውቅም። ምናልባት የሚፈራው እርሱን ስለሆነ ይሆንን ? እኔ እንጃ
✍️ ምን ለማለት ነው ? አሁን አሁን በጠያቂዎችም በተጠያቂ ዎች መካከልም በጣም ፍጥነት እየታየ ነው ። ሁሉ ጠያቂ ሁሉ መላሽ ሁኗል። ምድያው ስለ ተመቸን የጓሯችን መምህር ሁሉ እየጋበዝን ብዙ የትምህርት እንቅፋት እየወለድን ነው ። የድንግል ማርያም ነገር እጹብ ድንቅ ሁኖ ቢደንቀንም" አይ ልቡና፦ ወአይ ነቢብ ፤ ወአይ ሰሚዕ ተብሎም ይተዋል። የመንፈስ ቅዱስ እንዚራ የተባሉት በድኅንጻ መንፈስ ቅዱስ የተቃኙት እንዲህ እያሉ ካለፉት እኛም ለነገ የምንለው እና መምህሮቻችን ይምጡ የምንለው ትምህርት፤ እንዲሁም ግብር ልንገባበት የሚገባ ትምህርትም መኖር አለበት።
✍️ ሁሉ ለሁሉ የተገለጠ አይደለም።ሁሉም ለሁሉ የተሰወረ አይደለም። ሁሉ ለእርሱ ግልጥ የሆነለት እርሱ ደግሞ ለሁሉ ስውር የሆነ አንድ አካል ብቻ ነው ። እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። የተገለጠችልንን ለመናገር ብቅ ስንል ያልተገለጠልንን ነካክተን እየተመለስን ስለሆነ ብንታገስ አይሻልም ወይ?
✍️ የምናስተካክል መስሎን ሁላችንም ሞከረን ነበር። አሁን ግን በዛ።እየባሰም ሄደ። ስናክም ካቆሰልን፤ስንጠግን ከሰበርን፤ ስንደግፍ ከጣልን ብንታገስስ? እኔ እንደ መሰለኝ ወጣቶቹ መታገስ እና ማዳመጥ አለባቸው የሚለውን በቀዳሚነት ወስጄ" ነገር ግን በዩቲዩብ ፤ በፌስቡክ፤ በቲክቶክ እና በሌሎችም በይነ ምረብ ምድያዎችም በዚህ ዙሪያ መልስ የምንሰጥ የጉባኤ መምህራን ሰባክያንም ብናታገስ መልካም ይመስለኛል ።?ከራሴ ጀምሮ። ይህንን ያልኩት በጉባኤ ቤት መምልራን ደረጃ የተሰራጩ ልዩነቶች ደግሞ እያየን ስለሆነ ። እያደገ መጥቶ አስቸጋሪ ደረጃ የደረሰ መስሎ ስለታየኝ ነው።
✍️ የጉባኤ መምህራን ተሰብስበው ወደ ፊት ከሚያዩት ጉዳይ አንዱ ይሄ ቢሆንስ ?" አሸናፊ እና ተሸናፊ የሌለበት ጦርነት እንደሚባለው ባናስመስለውስ? አሁን የጥቅስ ጥይት ከመተኳኮስ ባለፈ በጥይቱ ድምጽጥ ልናደርገው የቻልነው ሀሳብ ብዙም የለንም። ማዶ እና ማዶ ሁኖ መተኳኮስ ችግሩ ይሄ ነው።ወይ ከተተኳኮሱ አይቀር የጨበጣ ቢሆን የሚያዘው ተይዞ፤የሚማረከው ተማርኮ።እጅ የሚሰጠው እጅ ሰጥቶ ፤ አሻፈረኝ ያለም ሙቶ አንድ ነገር ይሆን ነበር። አሁን ግን አቃራቢም አቀራራቢም አልተገኘም። ወጣቶቹን ለማስተካከል ስንል የእይታም ሆነ የምልከታ የአስተምህሮ ልዩነቶች የመሰሉ ሀሳቦች በጉባኤ መምህራኑ ዘንድም እየታዩ ናቸው ። የበደለውን ሥጋ፤ የጎሰቆለውን ፥ የኅጢአትን ሥጋ ተዋሐደ የሚል ቃል በቃል በሊቃውንት መጻሕፍት ተጽፎ ይገኛል። ነገር ግን ከምን አንጻር እንዲህ ተባለ?" ብሎ የተባለበትን ከመረዳት ይልቅ ትርጓሜውን አቅንተን በግላችን እንተረጉማለን ብለን እየሳትን ነው ። ወጣቶች ደግሞ አጠቃላይ በሥጋው ወራት የገጠሙትን መከራዎች ሁሉ በንዴት በጉቁልና በረኅብ በፍርኅት በድካም በኅሳር በሞት በስደት በለቅሶ የተገለጡትን ሁሉ ውድቀቶች መባላቸውን እነዚህም በጌታ መፈጸማቸውን በማየት ሥጋን ነስቷል በማለት ቦታ በደልንም ነስቷል እንዳንል መጠንቀቅ ግድ ይላል ። በበደል ምክንያት በእኛ የመጡ ቅጣቶች እነዚህን ቅጣቶች በእኛ ተገብቶ ፈጽሞልናል እንዳንልም ሌሎቻችን መጠበቅ ይገባናል። አሁንም ቃላቱ እያደጉ መጥተው ትምህርተ ሃይማኖቱን እየነኩት ነው ። ስለዚህ እንረጋጋ።
✍️ በዋናነት ሁሉም በአካባቢው ካለው ቲክቶከር ጋራ እየተገናኘ የግል ሀሳቡን የሚያሰራጭ ከሆነ እንደ አሸን የሚፈላ ችግር እንዳናመጣ እሰጋለሁ።መወያየታችን ለብዙዎች የእውቀት ፤የቤ/ክርስቲያኗን ጥልቅ ትምህርት፤ የነገረ ማርያምን ከባድ ምሥጢራት ያሳየና መጻሕፍትን እንድንዳስስ ያደረገ ቢሆንም እንኳን ምእመኑ ግን አሳዘነኝ። ትናንት አንድን መምህር ሰምቶ አሁን ነው የተረዳኝ ብሎ አመስግኖ ሲያበቃ ያንን ትምህርት ከመኖር ወደ አለመኖር ከምንት ወደ ኢምንት የሚቀይር መምህር መጥቶ ሲያከሽፍበት ምን ይሰማው ይሆን ? እና በእመን አምላክ እንታገስ።
✍️ መልስ መስጠቱን መቃወሜ አይደለም። የምእመኑ እሮሮ በዝቶ እያየሁ ነው። በአለት ላይ የተመሰረተ የማይነቃነቅ ሃይማኖት እንዳለን እናምናለን። በድንጋሌ ሕሊና ከመላእክት እንኳን የምትበልጥ እናት እንዳለችን እናምናለን። ዕለት ዕለት ውዳሴዋን ደግመን ቅዱስ ኤፍሬምን ፤ቅዳሴዋን ደግመን አባ ሕርያቆስን፤ አርጋኖኗን ደግመን አባ ጊዮርጊስን እንመስል ዘንድ መምሰልን ከፈጣሪዋ እንድታሰጠን የምንወዳት እናት አለችን ። በዚህ እንስማማለን ።
በሌሎችም እኛ እንጅ የቤ/ክርስቲያኗ ቋሚ አስተምህሮ የተስማማ ነው ። ስለዚህ እንታገስ። ምክንያቱም አሁን አሁን ከጉባኤ ቤታችን ክርክርም ወጣ ብሏል። በተለይ ለአባቶቼ የጉባኤ ቤት መምህራን እና የትርጓሜ ሊቃውንት አጭር ሀሳብ ልበል እና ልቋጫት ።
አንጽሓን ሳይጨምር ዐቀባን በተመለከተ የጉባኤ ቤቶቻችን ልዩ ልዩ እይታዎች እና አስተምህሮዎች አሉ።ከእናቷ ማኅጸን ጀምሮ ጠበቃት ማለትን እናቷ የተባለች ሔዋን ናት ። የለም ሐና ናት የሚሉ ።
2ኛ ንጽሕት ዘር ከአዳም ባሕርይ ተከፍላ ኅጢአት ሳይነካት በሴት አካል ተቀርጻለች የሚለውን ከዚያ ሲወርድ ሲዋረድ በኖኅ አካል ፤ ከዚያ በሴም፤ ከዚያ በአብርሃም፤ ከዚያ በይስሐቅ፤ ከዚያ በያዕቆብ፤ ከዚያ በይሁዳ ፤ እያለ በዕሴይ ፤በዳዊት አካል ፤ በሰሎሞን አካል ተቀርጻለች የሚለውን ሐተታ ቃል በቃል ሐተታውን በመያዝ ንጽሕት ዘር በዘር ውስጥ መርገም ኅጢአት ሳይነካት መጣች የሚል ሀሳብ አለ።

❤1👍1
3ኛ ከቀድሞ ጀምሮ የተጠበቀች ንጽሕት ደም ናት በማለት እመቤታችን ከቀድሞ አዳም ሲበድል ጀምሮ የተጠበቀች ንጽሕት ደም እንደነበረች በማስረዳት ከላይኛው ያልተለየ ሀሳብ ያላቸው አሉ።
4ኛ ከሁሉ ነገር የተጠበቀችው ከእናቷ ከሐና ነው አስቀድሞ የመጣ መርገም ያልነካው ዘር የሚባል የለም ። እርሷን ግን ከእናቷ ማኅጸን ኅጢአት ካመጣው ከመርገም ጠብቋታል ይላል። አጠቃላይ በዚህ ማኅቀፍ የሚታዩ ሰፊ እይታዎች ይኖራል። ይሄ ደግሞ ጉባኤ ተይዞለታል።ጉባኤው ለዚህ መፍትኄ ሰጭ ይመስለኛል።አሁን እየነካካን ባናቋስለው መልካም አይደለም??
መንፈስ ቅዱስ ዐቀባን በተመለከተ የጉባኤ ቤቶቻችን የአብነት እና የእይታ የምልከታ ልዩነቶች እንዳሉ ይታወቃል ። ይህንን እንመን።
ለምሳሌ "
መንፈስ ቅዱስ ከእናቷ ማኅጸን ጀምሮ ጠበቃት ብሎ አባ ጊዮርጊስ በአርጋኖን መጽሐፉ የገለጠውን እንደ መነሻ በመጥቀስ ከእናቷ ማኅጸን ጠበቃት በሚለው ሀሳብ የጉባኤ ቤቶች ልዩ ልዩ እይታ አለ።
1ኛ ከእናቷ ማኅጸን ስላለ እናቷ የተባለች ሔዋን ናት የሚል፤
2ኛ የለም በሔዋን ማኅጸንማ አላደረችም። እናቷ የተባለች ሐና ናት የሚል ነው ።
ከሔዋን ማኅጸን ጀምሮ የሚሉት አሸናፊ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ...የሚለውን የኢሳይያስን ጥቅስ በመያዝ ዘር የተባለች እመቤታችን ናት። ልክ ዛሬ ከአባት ዘር ከእናት ደም ተከፍሎ በእናት ማኅጸን ተዋሕዶ ሰው እንደሚሆነው እመቤታችን የምትገኝበት ዘር በአበው አብራክ ኅጢአቱ መርገሙ ሳይነካው መጥቷል የሚል ነው ።አስረጅ ስፍሆ ገብረን፤ ማርይምሰ ተሀቱን ይጠቅሳሉ። ይጠቅሳሉ ነው ያልኩት።
ሁለተኛው ክፍል" የለም " የተጠበቀች ከሐና ማኅጸን ጀምሮ እንጅ ከቀድሞ ጀምሮ የተጠበቀ ዘርም ደምም የለም ።
በአበው አብራክ እየተፍለቀለቀች ውስጥ ለውስጥ የመጣች ዘር ስንልም ሌሎችን መጠበቅ ግድ ይለናል ለማለት ነው ።
መምህር ጽጌ አስተራየ እንደጻፉት

👍1
የጎሠቆለ ባሕርይ (Fallen Nature)
ይህን ጉዳይ ትንሽ ዘርዘር አድርጎ ለመረዳት አዲሱን "ዐይነ ልቡና" የሚለውን መጽሐፌን ይመልከቱ። አምስት ኪሎ "ሰርዲኖስ የመጻሕፍት መደብር" ዋና አከፋፋይ ኾኖ በሌሎችም የመጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁና። ዛሬ በአጭሪ ላቀርብ ወዳሰብኹት ጉዳይ ልግባ።
የጎሠቆለ ባሕርይ የሚባለው በዋነኛነት አዳም ከበደለ በኋላ የኾነው ነው። አዳም ከውድቀቱ በኋላ የሰውነት ባሕርዩ አልተለወጠም። ከውድቀት በፊት ኾነ ከውድቀት በኋላ በሰውነት ለውጥ የለምና። ነገር ግን ከውድቀት በፊት በንጹሕ ባሕርይ መልክአ እግዚአብሔሩ ሳይደክም፤ የጸጋ ልብስን ለብሶ በፍጥረት ላይ የገዥነትን ሥልጣን ተጎናጽፎ በክብር ይኖር ነበረ። ሕገ እግዚአብሔርን ተላልፎ በወደቀ ጊዜ ግን የባሕርይ ውድቀት (ሕማም) ወይም ንዴተ ህላዌ (የባሕርይ ድህነት) ገጠመው።
- Fallen Nature በዋነኛነት የመልክአ እግዚአብሔር መድከምን፦ አዳም የተፈጠረው በእግዚአብሔር መልክ ነው። ያን በተፈጥሮ የተሰጠውን መልክአ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ባያጣውም በሕግ መተላለፉ ምክንያት አደከመው። አንዱና ዋነኛው የጎሠቆለ ባሕርይ ምልክት ይህ ነው። ኹለተኛው የጎሠቆለ ባሕርይ የሚባለው ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቆተ፦ ማለትም እግዚአብሔር አልብሶት የነበረውን የብርሃን ልብስ ያወለቀ፥ የእግዚአብሔር ልጅነትን ያጣ ባሕርይ ነው። ሦስተኛ ከባሕርዩ መጎሥቆል የተነሣ ለኃጢአት የሚያዘነብል መኾን ነው። አራተኛ ጉሥቁል ባሕርይ ያለው ሰውነት ርግማንን ተሸክሟል። ይኸውም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ነው። በሥጋው ወደ መቃብር ገብቶ መበስበስ (ሞተ ሥጋ)፤ በነፍሱ ወደ ሲኦል መግባት ነው (ሞተ ነፍስ) ዋናው ሞተ ነፍስ ከእግዚአብሔር መለየት ገጥሟቸዋል። ስለ ርግማን ሞት ስናነሣ በዋነኛነት የነፍስ ከሥጋ መለየትን ብቻ ሳይኾን የሥጋን ወደ መቃብር ገብቶ መበስበስ፣ የነፍስን ከእግዚአብሔር መለየት (ሞታ ለነፍስ ርሒቅ እም እግዚአብሔር እንዲል ሊቁ ቅዱስ ያሬድ) ይህን ይመለከታል። የሐዲስ ኪዳንን ሞት ለመረዳት "ዐይነ ልቡና" የምትለውን መጽሐፌን ይመልከቱ። እነዚህ በመሠረታዊነት ሰውነትን የጎዱና ያደከሙ ናቸው።
-በባሕርዩ መጎሥቆል ምክንያት የመጡ ጎጂ ያልኾኑ ኹኔታዎች ወይም ሕማማት ዘአልቦቱ ኃጢአት (blemeless Passions) ኃጢአት አልባ ሕማማትን መቀበል ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ተብሎ በፈቃዱ ለቤዛነት ብሎ የተቀበላቸው ናቸው፤ እመቤታችን ደግሞ ሰው እንደ መኾኗ ያን እንድትቀበል ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቅዷል። ስለዚህም ተርባለች፣ አዝናለች፣ ተሠቃይታለች፣ ሞታለች። እነዚህ ኹኔታዎች በራሳቸው ኃጢአቶች አይደሉም። እንደ ነውርና ርኲሰትም አይቆጠሩም። ጌታችንም እነዚህን ስለኛ ብሎ የተቀበለው በዚህ ምክንያትና ስለኛ ቤዛ ሊኾነን ነው። ይሄን የተቀበለው ደግሞ ሥግው ቃል እንደ መኾኑ ነው። ስለኛ መራቡን፣ መጠማቱን፣ መገረፉን፣ የእሾህ አክሊል መቀዳጀቱን፣ መራራ ሆምጣጤ መጠጣቱን፣ በመስቀል ላይ ዕርቃኑን መሰቀሉን፣ መሞቱን በእውነት የተቀበላቸው ቤዛ ሊኾነን እንጂ ያን በመቀበሉ ምክንያት የጎሠቆለ ባሕርይን ለብሷል ለመሰኘት አይደለም። ቃል ከሥጋ ከተዋሐደ በኋላ ሥግው እንደ መኾኑ ለቤዛነት የተቀበላቸውን ነገሮች የማዳን ሥራ (Economy of Salvation) እንላለን እንጂ በሌላ መንፈስ እንዲታይ ፈጽሞ አናደርግም።
እነዚህን ነገሮች ሥግው ቃል በፈቃዱ ያደረጋቸው ናቸው። ብዙ ቅዱሳን ሊቃውንትም ቅዱስ ቄርሎስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ... "ኅሥሩ" -"ጉሥቁል" ሥጋን ነሣ ሲሉ በአንድ በኩል ከደካማው አዳም ሰውነት የተከፈለውን ሰውነት መንሣቱን ለማሳየት ሲኾን በሌላ በኩል በፈቃዱ ሕማም፣ መከራና ሞት የሚስማማውን ሰውነት ገንዘብ ማድረጉን ለማመልከት ነው። ከዚህ ውጭ ከላይ በዋነኛነት የወደቀ ባሕርይን የሚገልጡ ነገሮች ያሉበትን ሰውነት ለበሰ ለማለት አይደለም። ለዝርዝሩ "ዐይነ ልቡናን" ይመልከቱ። በነገራችን ላይ አኹን እንኳን እኛ ኦርቶዶክሳውያን አምነን፣ ተጠምቀን በቅብዐ ሜሮን ከብረን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን የክርስቶስ አካል ከኾን በኋላ blemeless passions የሚባሉት ያልቀሩልን በራሳቸው ክፉዎች ስላልኾኑ ነው። እነዚህ ነገሮች አዲስ ሰውነትን ገንዘብ አለማድረግን የሚያመለክቱ አይደሉም። ይኸውም ማለት በጥምቀት ከአሮጌ ማንነት ወጥተን ክርስቶስን ለብሰን አዲስ የምንኾን መኾናችንን የሚያስቀሩ አይደሉምና። ከአሮጌ ማንነት በጥምቀት ከተላቀቅን በኋላ መልሰን ባረጀ ሰውነት ውስጥ እንዳለን አድርገን አንናገርም። በትንሣኤ አኹን ከለበስነው የበለጠ የከበረ ኢመዋቲ ኢድኩም ወኢሕሙም የኾነ ሰውነትን መልሳችንን ፍጽሙ ድኅነት ከትንሣኤ በኋላ መኾኑን የሚያረጋግጥ እንጂ አኹን ብትጠመቁም አሮጌ ማንነት ውስጥ ነው ያላችሁ የሚያስብል አይደለም። ሌላው ቀርቶ ያን አዳም በገነት እያለ ያወለቀውን የብርሃን ልብስ ስንጠመቅ እንለብሰዋለን (በተለይ ቅዱስ ኤፍሬምና ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በትኩረት ይህን ያስተምራሉና) ነገር ግን ለኛ ለዐይነ መጭማጮች ከተጠመቅንም በኋላ ያን የብርሃን ልብስ መልበሳችን አለመታየቱ ያለመልበሳችን ማረጋገጫ ሊኾን አይችልም። ነገር ግን በግልጽ አኹን ያን ልብስ መልበሳችንን ማየት ባንችልም ከትንሣኤ በኋላ ተገልጦ እናየዋለን። ያኔ የሚገለጠው ግን ላልተጠመቁ ሳይኾን በጥምቀት ለከበሩት ክርስቶስን ለለበሱ ነው። ይህን ልብ ማለት ይገባል።
- አካላዊ ቃል የተዋሐደው ሥጋ ንጹሕ ሥጋ ነው። ምንም ዓይነት ነውርና ነቀፋ የለበትም። መንሣትና መዋሐድ ያለመቀዳደም የኾነ ስለ ኾነ ከእመቤታችን የነሣው ሰውነት ንጹሕና ነውር ነቀፋ የሌለበት ነው። የኃጢአት ጠባሳም አላገኘውም። ጸጋን የተመላ፣ መልክአ እግዚአብሔሩ ያልደከመ፣ ኃጢአት ያልገዛው፣ መርገም ያላረፈበት ንጹሕ ሰውነት ነው። ቅድስት ድንግል ማርያም የተጠበቀችው የጉሥቁልና ውጤት ከኾነው ከጸጋ መራቆት፣ ከመልክአ እግዚአብሔር መድከም፣ ለኃጢአት ከማዘንበል፣ ከመርገመ ሥጋ ወነፍስ፣ ከልማደ አንስት በወሊድ ጊዜ ከሚመጣ ምጥ ኹሉ ነው። ይህ ከእርሷ በቀር ከሰው ወገን ለማንም ቀድሞ የተደረገ አይደለም። ስለዚህም ምክንያት በዋነኛው የውድቀት ምልክት አንጻር አድርገን ስናይ እርሷ የወደቀ ሰውነትን ገንዘብ እንዳታደርግ ልጇ ጠብቋታል እንላለን። የእርሷን ሕይወት በልዩ ኹኔታዎች እንዲመላ ያደረገው እርሱ አምላኳ ነውና። የጎሠቆለ ሰውነትን አልለበሰችም ስንል ሕማም፣ ኀዘን፣ መከራ፣ ሞት የማይስማማውን ሰውነት ገንዘብ አድርጋለች ማለታችን አይደለም። ይህን የሚልም አይኖርም ይልቅስ ከላይ እንዳልኹት ከዋነኛው የጒሥቁልና ውጤት መጠበቋን ማዕከል በማድረግ የወደቀ ሰውነትን አልለበሰችም እንላለን። አበውም ያስተማሩት በዚህ አግባብ ነው። በዝርዝር የእርሷን ጉዳይ ለመረዳት "ዐይነ ልቡና" ይነበብ። ልጇ በፈቃዱ ስለኛ የሞተው በማስመሰል ሳይኾን በአማን ነው። ሞትንም በፈቃዱ የተቀበለው ያ ሥጋ የዕሩቅ ብእሲ ሥጋ ሳይኾን የሥግው ቃል ሥጋ ነውና። ሞትን ስለኛ የተቀበለው ሥጋ ራሱ ለኛ ሕይወትን የሚያድል ነው። የሞተውም ሊበሰብስ ሳይኾን ሞትን በሞቱ ገድሎ ሞት የወረሰውን ሰውነት ሕይወት ሊያለብሰው ነው። ይህ የቅዱስ አትናቴዎስና የቅዱስ ቄርሎስ የትምህርት ማዕከል ነው።
እመቤታችን ለምን ሞተች? መልሱ በአጭሩ፦

1) የሞተችው ለመበስበስ ሳይኾን የትንሣኤን አካል ገንዘብ ለማድረግ ነው። ይኸውም ኢመዋቲ አካልን ገንዘብ ለማድረግ እንጂ ለመበስበስ አይደለም። ይህ ዮሐንስ ዘደማስቆ በመደነቅ የገለጸው ነው። ሰውነቷ እንዲበሰብስ ልጇ አለመፍቀዱን ሞታ መበስበስ ሳያገኛት ከልጇ ትንሣኤ በኋላ በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን መነሣቷን ብዙዎቹ ቅዱሳን ሊቃውንት የገለጹት እና እኛም የምናምነው ነው።
2) የሞተችው ሰው ስለ ኾነች ነው። አምላክ በመውለዷ ምክንያት በሕሊናቸው ሰው አይደለችም የሚሉ ሰዎች እንዳይኖሩና በእርሷ ሰው የመኾን ጉዳይ ጥርጣሬ እንዳይፈጠር ሞትን ትቀምስ ዘንድ ልጇ ፈቅዷል። ይህ እነ አብሮኮሮስ በአጽንዖት ያስረዱት ነው። ይህ ምክንያት ቃል ሰው አልኾነም የሚለውን ክሕደትናና እርሷም ሰው አይደለችም የሚለው ስሕተት የሚያርም ነው።
3) ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ያረፈችው የልጇን የሞት ጽዋ ለመቅመስ ነው። ይህም እንዲኾን የእርሱ ፈቃድ ነው።
4) ሞቷ የመሸነፍ ሳይኾን የክብር እና የድል እንደ ኾነ እንድናውቅ ነው። ይህን ለመረዳት የሞቷን ዜና ከልጇ ዘንድ የተላከው ቅዱስ ገብርኤል ሊያበሥራት ሲመጣ የድል ምልክት የኾነውን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ መምጣቱን እነ ማክሲሞስ ተናዛዚው የቀደሙ ትውፊቶችን ማዕከል አድርገው "The Life of The Virgin" በሚለው መጽሐፍ ዘግበዋልና።
5) ሞቷ ተራ ሞት ሳይኾን በመደነቅና በመገረም የሚናገሩት ሞት ነው። ቅዱስ ያሬድ "ማትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኲሉ" - ሞትማ ለሚሞት ይገባል የማርያም ሞት ግን ለኹሉ ያስደንቃል" የሚለው ለዚህ ነው። እንደ በሥጋና በደም ኾነን በድፍረት ከመናገር ልንቆጠብና ልናደንቅ ይገባል።
ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው እንደጻፈው

1) የሞተችው ለመበስበስ ሳይኾን የትንሣኤን አካል ገንዘብ ለማድረግ ነው። ይኸውም ኢመዋቲ አካልን ገንዘብ ለማድረግ እንጂ ለመበስበስ አይደለም። ይህ ዮሐንስ ዘደማስቆ በመደነቅ የገለጸው ነው። ሰውነቷ እንዲበሰብስ ልጇ አለመፍቀዱን ሞታ መበስበስ ሳያገኛት ከልጇ ትንሣኤ በኋላ በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን መነሣቷን ብዙዎቹ ቅዱሳን ሊቃውንት የገለጹት እና እኛም የምናምነው ነው። 2) የሞተችው ሰው ስለ ኾነች…
ጥቅስን ማንም አንባቢ ይጠቅሰዋል፡፡ በልኩና በዐውዱ መረዳት ግን ለኹሉም አይደለም፡፡ ዐይነ ልብ ላላቸው ብቻ ነው፡፡
ስለ አንዱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለም መግባባት ያልቻለው ኹሉም እንደ ፍላጎቱ መጽሐፍ ቅዱስን ስለሚጠመዝዘው ነው፡፡
መጻሕፍት ሲነበቡ ቢያንስ ከ Textual Analyisis; comparativ Study; Historical Context አንጻር ማየትግዴታ ነው፡፡ ዐውቀንም ይኹን ሳናውቅ በእኛ ዘንድ Eisegetical reading/ንባብን በራስ ፍላጎት ብቻ መቆልመም ከተለመደ፥
ቅድስት ቤተክርስቲያን ነገ በእጅጉ ትፈተናለች፡፡
በሰሞነኛው ውርክብ ዙርያ ይኽን የወንድማችንን መጽሐፍ ማንበብ፥ መደበኛውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ለማወቅ ያግዛል፡፡
ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው

👍2
የአክሊል ችግር ምንጩ ምንድነው?
...
ወንድማችን አክሊል ወደ አገልግሎት መመለሱ መልካም ነው፤ እግዚአብሔር የሰጠውን ጸጋ ለመጠቀምና ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት ለማዋል ማበረታታት አለብን። እኔ በትጋቱና በብዙ መንገድ ምእመናንን እየጠቀመ ላለው አገልግሎቱ አድናቆት አለኝ። አድናቆቴን ከምገልጥባቸው መንገዶች አንዱ ስሕተት ሳይ እንዲያስተካክል መምከር እንቢ ካለም የሚሰሙት እንዳይሳሳቱ ማስተማር ነው።
....
በትጋት ሲያገለግል ምርቃትና ድጋፍ እንደሚሰጠው ሁሉ ስሕተት ሲሠራም ለመታረም ፈቃደኛ እንደሆነ እገምታለሁ፤ ለመታረም ፈቃደኛ ነኝ ብሎ ሲናገርም ስለሰማሁት ስሕተት የማይሠራና የማይታረም አድርጎ ራሱን አይቆጥርም ብየ አምናለሁ።
...
ከዚህ ቀደም ያሉኝን ልዩነቶች አገልግሎታችንን በማይጎዳና ፍቅርን መሠረት ባደረገ መንገድ አስተያየት ሰጥቻለሁ። አስተያየቶቼ ይዘትንም አካሄድንም የሚመለከቱ ነበሩ፤ በዚህ ጽሑፍ ግን መታረም አለመታረማቸውን መገምገም አልፈልግም።
....
አክሊል በቅርቡ በቪዲዮ ያስተላለፈውን መልእክት ሁለት ጊዜ ሰማሁት፤ አንድ ጊዜ የሰማሁት ሌሊት ከ9:30-10:35 ነው። ይህ ጊዜ ጸጥታ የሰፈነበት ስለሆነ በትክክል ሰምቼዋለሁ። ስሕተት ነው ብየ ያመንሁትን ነጥብ የለየሁት በዚህ ጊዜ ነበር። ተመልሼ ስሰማው ማስታወሻ ይዤ ቪዲዮ በየስፍራው እያቆምሁና መልሼ እያዳመጥሁ ነበር።
...
"ያልነሣውን አላዳነውም" የሚለው ርእስ የታወቀና የታመነ ንባብ ነው፤ የነሣውን በትክክል ዐውቀን በትክክል እየገለጥነው ነው ወይ? የሚል ጥያቄ ግን አለኝ።
...
ጥቅሱን ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንደተረዳውና እንደተጠቀመው ተረድቻለሁ። እንደ አቻዎቹ ያለ ሥጋን ይዟል እያለ ደጋግሞ ይናገራል። የአክሊል እንደ አቻዎቹ ያለ ሥጋ ማለት ምን ማለት ነው? የአቻዎቹ ማለት የሁላችንም ሰዎች ሥጋ ማለት ነው። ክርስቶስ ገንዘብ ያደረገው ሥጋችንን ወይም ባሕርያችንን ነው። ባሕርያችን በተፈጥሮ አንድ ነው። የእኛ ሥጋ ኀጢአተኛ ሥጋ/ባሕርይ ግን መሆኑን አክሊልም አይክድም። የጌታ ሥጋም እንደ አቻዎቹ ያለ ሥጋ ከሆነ ኀጢአተኛ ሥጋ (ባሕርይ) ነው ማለት ነው? ይህን እያለ ከሆነ ስሕተት ነው። ቢያንስ ይህን አጥርቶ መናገርና ሰሚን ከማደናገር መታቀብ አለበት። የጌታ ሥጋ እንደ ሁላችንም የሰው ልጆች ሥጋ ነው። ይህም ማለት ሞት የሚስማማው ሥጋ ነው ማለት ነው። መዋቲነት፣ መታመም፣ መራብና መጠማት፣ መድከም እነዚህ ሁሉ የሥጋ (የሰው ባሕርይ) ገንዘቦች ናቸው እንጂ በኀጢአት ምክንያት በኋላ የመጡ አይደሉም።
....
የሳዊሮስና የአትናቴዎስን ትምህርት በትክክል ካነበበ መዋቲነት የሰው ተፈጥሮ ገንዘብ እንጂ የኀጢአት ውጤት አይደለም። ዲያቆን ያረጋል በተረጎመው የቅዱስ አትናቴዎስ መጽሐፍ ገጽ 160 ላይ
"ሕጉን መተላለፍ ሲጀምር ሰውን በባሕርዩ የነበረ መዋቲነትና መለወጥ (moryality and corruptibility) ገንዘቡ አድርጎ ወርሶታል" ይላል። በቅዱስ ሳዊሮስና በቅዱስ አትናቴዎስ ትምህርት መሠረት ሞት እንጂ መዋቲነት የኀጢአት ውጤት አይደለም። መዋቲነትና መለወጥ (mortality and coruptibility) የሰው የባሕርይ ገንዘቦች ናቸው። ኢመዋቲነትና አለመለወጥ ( immortality and incorruptinility) ደግሞ የእግዚአብሔር ብቻ የባሕርይ ገንዘቦች ናቸው። እግዚአብሔር ሰውን ኢመዋቲ ሊያደርገው ፈቃድም ችሎታም አለው እንጂ ኢመዋቲ አድርጎ አልረጠረውም።
....
አክሊል በሁሉም ንግግሩ ውስጥ ደጋግሞ ስለጌታ መዋቲነት ሲናገር በኀጢአት ምክንያት በሰው መዋቲነት እንደመጣበትና ጌታም ያን ገንዘብ እንዳረገ አስመስሎ ይናራል። ይህን ነጥብ ለብዙ ትምህርቱ ምንጭ አድርጎ እየተጠቀመው ስለሆነ አጥርቶ መረዳትና ማረም አለበት።
.....
ጌታ ሥጋን ገንዘብ ያደረገው ፦ በተፈጥሮው መዋቲ ከሆነ፣ በኋላም በኀጢአት ወድቆ ሞት ከሰለጠነበት ሥጋ ከፍሎ በሥጋዌ ምሥጢር በግብረ መንፈስ ቅዱስ በዐዲስ መልክ በድንግል ማርያም ማኀፀን የተፈጠረ ሥጋን እንጂ ሞት የሰለጠነበትን ባሕርይ ከሞት ነጻ ሳያወጣ አይደለም። በፈቃዱ ለሌሎች ቤዛ ሆኖ ከመሞት በቀር በጌታ የግድ ሞት የሌለበት በተፈጥሮው መዋቲነት ገንዘቡ የሆነ እንጂ ሞት በኀጢአት ምክንያት ያልሰለጠነበት ሥጋን ገንዘቡ በማድረጉ ነው።
...
የእኛ ሥጋ በተፈጥሮው ከጌታ ሥጋ ጋር አንድ ብቻ አይደለም። በኀጢአተኛነቱና ሞት የሰለጠነበት በመሆኑም የተለየ ነው። የጌታ ሥጋ መዳንን የማይፈልግና ከቃል ጋር በመዋሐዱም አዳኝ ነው። ይህን ነጥብ አክሊልም በስሱ አንሥቶታል። ነገር ግን በጉሕህ መነሣት ያለበት ይህ ልዩነትም እንጂ ባሕርያዊ አንድነቱ ብቻ አይደለም። የጌታ ሥጋ እንደ እኛ ነው ብለን በደፈናው ብንሰብክማ ሞት ችግር ያመጣል። ጌታ ሥጋችንን ሲዋሐድ የሰውን ባሕርይ ከኀጢአት በፊት ወደ ነበረው ክብር ብቻ ሳይሆን ወደማይነገር ታላቅ ክብር ያወጣው መሆኑን አክሊል ከተናገረውም ይገኛል።
....
ሳዊሮስና ዩልያኖስ የተለያዩበት ነጥብ ሰው ከኀጢአት በፊት መዋቲ ነው/አይደለም የሚል ነበር። ዩልያኖስ መዋቲ አልነበረም። ኢመዋቲ ነው ብሎ አስተማረ። ሰው ኀጢአት ሲሠራ መዋቲ ሆነ አለ። ስለዚህም ጌታ የለበሰው ሥጋ አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረው ሥጋ ነው። ሞት አይስማማውም። የሞተውም በፈቃዱ ነው እንጂ የሚስማማው ሥጋ ስላለው አይደለም አለ። መዋቲነት የኀጢአት ውጤት ነው ብሎ ማመኑ ጌታ መዋቲ ሥጋን ሊዋሐድ አይችልም እንዲል አደረገው። ሳዊሮስ ግን መዋቲነት የሰው ተፈጥሮ ገንዘብ እንጂ የኀጢአት ውጤት አይደለም። የኀጢአት ውጤት ሞት እንጂ መዋቲነት አይደለም አለ። ልዩነቱ ካልገባን ቀጣይ አጽፋለሁ።
...
ጌታ ሰው ሲሆን መዋቲ ሥጋን ገንዘብ ማድረጉ የሰውን ተፈጥሮ መዋሐዱ ነው። ነገር ግን የአዳም ባሕርይ መዋቲነቱ ኢመዋቲ የመሆን እድል ነበረው። ይህን እድል በበደለ ጊዜ አጣ። በቅዱስ አትናቴዎስ አገላለጽ ኀጢአት የነበረውን እድል ማጥፋትዋ ብቻ ሳይሆን ሰውን ወደ አለመኖር እንዲመለስ ጉዞ አስጀምራው ነበር። ኀጢአት የሰውን ክብርና እድል ብቻ ሳይሆን ህልውናውን ለማጥፋት ጉዞ አስጀምራው ነበር። ነገር ግን የፈጠረን እግዚአብሔር ራራልንና ከጥፋት መንገድ መለሰን።
...
ጌታ መዋቲነትን በተዋሕዶ ጊዜ ያላጠፋው ስለማይችል ሳይሆን እንዲያድንበት ፈልጎ እንዳይጠፋ ስለፈቀደ ነው። ሞትን በፈቃዱ ለመቀበልና በእርሱ ሥጋ ለማጥፋት መዋቲነቱ መቆየት ነበረበት። መዋቲነቱን በተዋሕዶ ጊዜ ከራሱ ሥጋ ላይ ካጠፋው እርሱ ኢመዋቲ ይሆናልና ሞቶ ቤዛ ሊሆነን አይችልም። "በሞቱ ለሞት ደምሰሶ" እንዳለው ሞትን አግኝቶ ሊውጠው ወይም ሊያጠፋው አይችልም። ሞት ጌታን መያዝና ማጥፋት አይችልም። እርሱ ንጹሕ ነውና በፈቃዱ ካልሆነ ሊይዘው አይችልም። በፈቃዱ ሊይይዘው የቻለው ደግሞ ሞትን ለማጥፋት ራሱ ስለፈለገ ነው እንጂ ሊሞት ስለተገደደ አይደለም። ይህ ነጥብ በአባቶች ትምህርት በዝርዝር የተገለጠ ነው። አትናቴዎስና ሳዊሮስ ደግሞ ይበልጥ አብራርተውታል።

በዚህ ጊዳይ ላይ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ነገር ለጊዜው አክሊል ማብራሪያ ውስጥ ያለው ችግር መዋቲነትንና መለወጥን (mortalility and corruptibility) ጌታ ስለተዋሐደው ሥጋ ስንናገር የኀጢአት ውጤት የሆነ ሞትና ጉስቁልና አድርጎ ማቅረቡ ይታያል። ይህ የኔ እይታ ብቻ ከሆነና ራሱም ሆነ ሌላ ሰው እይታየን እንዳስተካክል ከረዳኝ አርማለሁ። የአክሊል መልእክት በሚዲያ የተላለፈ ስለሆነ እንጂ ጉዳዩን በሚዲያ ማንሣት ያለውን ጣጣ እረዳለሁ። በፍቅርና በእውነት ቤተ ክርስቲያንን ማእከል አድርገን ደግሞም ራሳችንንና የሚሰሙን ለማነጽ ከተነጋገርን ችግር አያመጣምና በዚህ መንፈስ እዩልኝ።
ሰላም ለሁላችን ይሁን!
መጋቤ ብሉይ አዕመረ አሸብር እንደጻፉት

👍1👏1
................የአክሊል ጉዳይ "..............
መፍትኄ ብትሆን ብየ ነው። አስተምህሮ ከሚለጠጥ
ከላይ የምንሰማው አንድ ድምጽ የለንም?
ስለ ወንድማችን አክሊል ቲክቶከሩም ፤ ዩትዩበሩም ልጁ ያለውንም ያላለውንም እየጨመረ እያውራ ሰዎች ከሚጨነቁ ፤ አስተምህሮዎችም በሆነ ባልሆነው ከሚንገላቱ አጭር መፍትኄ የለንም እንዴ ? አንዳንዴ የገበያ ግር ግር ለቀጣፊ ይመቻል እንዳይሆን እና ምናልባት ጉዳዩን አዠንዳ አድርጎ የሰጠን ይኖር ይሆን?ብሎ ቆም ብሎ ማሰብም ተገቢ ይመስለኛል ።
1ኛ የሊቃውንት ጉባኤ ውስጥ የሚሰሩ አባቶቻችን ልጁን ቀን ሰጥተው ፤ በፍቅር ጠርተው እርሱም ተዘጋጅቶ ፦ ከጉባኤ መምህራንም ፤ ከቲኦሎጅ መምህራንም ፤ በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ከሚያገለግሉ ከምናውቃቸው ታላላቅ መምህራንም በቅርቡ ያሉ
አንድ ስድስት መምህራን ተጠርተው ሀሳቡን አቅርቦ በመጽሐፍ ቅዱስ ፤ በአበው አስተምህሮ ታይቶ ተመርምሮ
ባቋጭስ? ምክንያቱም እርሱም ለመታረም ዝግጁ ነኝ ያለ መስሎኛል ። ከአካሄዱ ጀምሮ የሚታረመውን አርሞ ፦ ልክ የሆነውን ልክ ነው ብሎ ፦ ልክ ያልሆነውን ሕዝቡ ሲሰማው ስለቆየ እርሱም እራሱ በራሱ ምክንያት አንድ ሰው ቢሰናከልበት ስለሚያስጠይቀው ፈቃደኛ ሁኖ ተወያይቶ ቢዘጋ ምን ችግር አለው ?
የሊቃውንት ጉባኤ አባላት አባቶቻችን ጉዳዩ ከሆነች ጎጆ ውስጥ ያሉ ሰዎች ጩኸት ብቻ አይደለም። ከሀገር ውስጥ እስከ ሀገር ውጭ ደርሷል። ይህንን አዠንዳ ማስተካከል እንዴት ተሳነው? ለልጁም ለቤተ ክርስቲያኗም እረፍት ነው። ሁሌም ከኔ ጀምሮ በያንዳንዱ አፍ ሲባረክ ሲረገም ከሚውል " እራሱ በተገኘበት ውይይቱ ሲጠናቀቅ ራሱም በዚህ ሀሳብ ልክ አይደለሁም እንዲል። ልክ የሆነበት ሀሳብ ደግሞ ይሄ ሰዎች እያጣመሙበት ወይም ያለ መረዳዳት ችግር እንጅ ልክ ነው ቢባል ምናለ?
↗️ ለቤ/ክርስቲያኗም ለምእመንም እኮ እረፍት ነበር ።እኔ ምድያ ላይ ተወያይቶ ከወደታች የኮሜንት በረዶ እየወረደ ምድያ ላይ ችግርን ማረምም ሆነ ማስተካከል የሚቻል አይመስለኝም ። የሀሳቡን ልብም ማግኘት አይቻልም። ምድያ ላይ የተሰራጨን ሁሉ በዚያው በምድያ ማስተካከል ጥሩ ነው። ነገር ግን ለማስተካከል ይ
የምንጓዝበትን ጉዞ ሁሉ በምድያ ማድረጉ አግባብ ውጤታማ አይመስለኝም። መፍትኄው ከተገኘ እና ከመረዳዳት በኋላ ከጅግሩ እስከ መፍትኄው በምድያ ማቅረብ የበለጠ ነው።ችግሩን ለይቶ ለማወቅም ለማሳወቅም ከዚያው ምድያ ላይ ከሆነ ግን ችግርን ጨምሮ ያርፋርል እንጅ ችግርን አይፈታም ።
↗️ በአጭሩ የሚቋጭ ቢሆን የእስከ ዛሬው የመምህራኑ ጥረት በቂ ነበርና። ለሁሉም ይህ ሁሉ ክርክር ለምን መጣ? ብላችሁ የምትደነግጡ ? የምትሸበሩ ምእመናን ትኖሩ ይሆን? ይህ የሆነው ሃይማኖታችሁ ድንቅ እጹብ ቢሆን ነው። የማርያም ነገር እንዲህ ነው ።መላእክት እንኳን ተጨምረው ቢያስቡት በእርሷ የተከናወነው ምሥጢር ክቡድ ነው። ሃይማኖታችሁ እንዲህ ነው።የማርያም ነገር ዛፎች ተሰብስበው ስለ እርሷ ቢያጨበጭቡ!! ተራሮች ተከማችተው ስለ ክብሯ ቢዘምሩ" የራሳችን ጠጒሮች አንድ ሁነው ቢያሸበሽቡ የማርያም ነገር የድንቅ ድንቅ ነው። ሃይማኖታችሁ ተራ ተረት ተረት አይደለም። ከሕሊና በላይ ነው።የማርያም ነገርም እንዲሁ ነው። ወላዕለ ኲሉ ሕሊና አይደለች። ማርያም ታማልዳለች አታማልድም ማለት ብቻ ሳይሆን በነገረ ድኅነት ያላት ድንቅ ሱታፌም እንደ ፋና ሲያበራ ይታያል።
አንድ ሊቅ ባለፈው በየ ዘመኑ በጥባጭ ጸሐፊ በጥባጭ ሊቅ መነሳት አለባት ያሉት ትዝ አለኝ። በጥባጭ መናፍቅ አይነሳ እንጅ በጥባጭ ሊቅማ ይነሳ። እንዲህ ያነቃቃልና። በስንፍና የረጋውን ሁከት መንፈሳዊ ሰጥቶ ይቀሰቅሰዋልና።
መምህር ጽጌ አስተርአየ እንደጻፉት

❤3👍1