Telegram Web
ታላቅ የምሥራች እነሆ። በቀሲስ ዶክተር መብራቱ መጽሐፍ ተዘጋጅቶልናል። አኰቴተ ቍርባንን ያነበበ ይህን ለማንበብ ምን ያህል እንደሚቸኩል አልጠራጠርም።

+ ካልእ መጽሐፍ በእንተ ቅዳሴ

በልዑል እግዚአብሔር ቸርነት "ቅዳሴ፡ ወደ ጌታ ደስታ የመግባት ምሥጢር" በሚል ርእስ በቅዳሴአችን ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ ጽፌአለሁ፡፡ በያዝነው ዐቢይ ጾም ለንባብ ይበቃል፡፡ መጽሐፉ በዋነኝነት ለማን እንደተጻፈና የተጻፈበትን ምክንያት ለማወቅ ለቅምሻ ያህል ከሥር ያለውን መቅድም ይመልከቱ፡፡

ምስጋና
አኰቴተ ቊርባን በሚል ርእስ የታተመው መጽሐፌ አራተኛ እትም አንድ ኮፒ ሲደርሳቸው መጽሐፉን በሚገባ አንብበው፣ “ይህ መጽሐፍ ለቤተ ክርስቲያናችን ካህናት በተገቢው መልኩ መዳረስ አለበት” በሚል መንፈሳዊ ቅንዐት (ተነሳሽነት) አምስተኛው እትም (1000 ኮፒዎች) በራሳቸው ወጪ San Diego, California ውስጥ እንዲታተም ላደረጉትና እርሳቸው በሚያገለግሉበት ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ካህናት በሙሉ መጽሐፉን በነጻ በማደል እውነተኛና ወንድማዊ ፍቅራቸውን ያሳዩኝን መልአከ ብርሃን ቀሲስ ማንችሎት ገበየሁን (በአትላንታ የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ) በምን አይነት ቃላት እንደማመሰግን አላውቅም፡፡ መንፈሳዊ ፍቅርን ለደቀ መዛሙርቱ “አዲስ ትእዛዝ” አድርጎ የሰጠ ጌታ (ዮሐ. 13፡ 34-35) ለቀሲስ ማንችሎት ፍቅረ ቢጽን አብዝቶ እንዲያድላቸውና ባለቤታቸውን ከነልጆቻቸው እንዲባርክላቸው ከመመኘት በስተቀር ከዚህ የተሻሉ ቃላት ማግኘት አልቻልኩም፡፡

ከአኰቴተ ቊርባን መጽሐፍ ሳንወጣ፣ የመጽሐፉን አንድ ኮፒ ስሰጠው “ተጨማሪ መጽሐፎችን መጻፍ አለብህ” ከሚል መልእክት ጋር ለዚሁ ሥራ የሚሆን laptop ገዝቶ ያበረከተልኝን፣ የቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትጉህና ቅን አገልጋይ የሆነውን ቴዎድሮስ መብራቱን አመሰግናለሁ፤ የበጎ ሥጦታዎች ሁሉ ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቡን በሰማያውያንና ምድራውያን በረከቶቹ ይባርክለት ለማለት እወዳለሁ፡፡
በዚህ መጽሐፍ መቅድም በዝርዝር እንደተገለጸው ለዚህ መጽሐፍ መዘጋጀት ምክንያት የሆኑት ሲሳይ ደምሴ (የበገና መምህር) እና ብሌን ታከለ (ዘቶሮንቶ መንበረ ብርሃን) በያሉበት ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡ በተጨማሪ፣ ብሌን በምእመናን ቦታ ሆና የመጽሐፉን ረቂቅ በደስታ በማንበብና ገንቢ አስተያየቶችን በፍጥነት በመስጠት ታላቅ አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡ “በጎ ስጦታ ሀሉ፣ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው . . . ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ” ተብሎ እንደተጻፈ (ያዕ. 1፡17) ካሰብነው በላይ በመስጠት ሁሌም የሚያስደንቀን አምላካችን የልቧን መሻት ይፈጽምላት፡፡

የአርጋኖን መጻሕፍት መደብር ባለቤት የሆነው አብርሃም (ክፍሎም) ኃይሉ በቅዳሴ ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ የመጻፍ እቅድ እንዳለኝ፣ ነገር ግን የኅትመቱ ውጣ ውረድና የሥርጭቱ ጉዳይ ልቤን እንደሚያዝለው ስነግረው፣ “አንተ ጻፍ እንጂ ለኅትመቱና ለሥርጭቱ እኛ አለን” በማለት ብርታትና ጉልበት ስለሆነኝ በጣም አመሰግናለሁ፤ እንደ አብርሃም ያሉ በጎ እና ቅን አገልጋዮችን ያብዛልን፡፡

በመጨረሻም፣ ለቅዳሴ ልዩ ፍቅር ያላት ውዷ ባለቤቴ ሔለን (ወስመ ጥምቀታ “ፍቅርተ ኢየሱስ”) በቅዳሴ ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ እንደምጽፍ ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ለዚህ መጽሐፍ ዝግጅትና ለተለያዩ የአገልግሎት ጉዳዮች በቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቢሮ ውስጥ ረጅም ሰዓታትን በማሳለፍበት ወቅት የልጆቻችንን (ዮሐና እና ሳሙኤል) የትምህርት ሂደት በትጋት በመከታተልና የቤታችንን ሸክም በመሸከም አገልግሎቴን ትደግፍ ስለነበር ልትመሰገን ይገባታል፡፡ እነዚህን ሁሉ በረከቶች ላበዛልኝ፣ በምሕሩቱ ባለጸጋ ለሆነው ሕያው አምላካችን ክብር፣ ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ ይሁን፡፡

ማውጫ
• መታሰቢያ
• ምስጋና
• መቅድም፡ ምክንያተ ጽሒፍ
• መግቢያ፡ በደስታ የተሰበሰቡ አእላፍ ቅዱሳን

ክፍል ፩፡ ወደ ቅድስናው ምስጋና የመግባት ዝግጅት

† ቡራኬ 1፡ የሰማያዊ ሠርግ ጥሪ
† ቡራኬ 2፡ ግብአተ መንጦላዕት: የዝግጅት ጸሎት
† ቡራኬ 3፡ ቤተ ልሔም
† ቡራኬ 4፡ ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት
† ቡራኬ 5፡ አግብኦተ ግብር
† ቡራኬ 6፡ አሐዱ አብ ቅዱስ . . .
† ቡራኬ 7፡ በእንተ ቅድሳት

ክፍል ፪፡ የቃሉ ትምህርት

† ቡራኬ 8፡ የሐዋርያት መልእክታት ምንባብ
† ቡራኬ 9፡ ዝ ውእቱ ጊዜ ባርኮት
† ቡራኬ 10፡ ሠለስቱ ቅዳስያት
† ቡራኬ 11፡ ነዋ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት
† ቡራኬ 12፡ ፃኡ ንኡሰ ክርስቲያን
† ቡራኬ 13፡ ጸሎተ ሃይማኖት
† ቡራኬ 14፡ ተሐፅቦተ እድ እና አምኃ ቅድሳት

ክፍል ፫፡ አኰቴተ ቊርባን፡ የአማንያን ቅዳሴ
† ቡራኬ 15፡ አልዕሉ አልባቢክሙ
† ቡራኬ 16: ጸሎተ አኰቴት፡ መቅድመ አኰቴተ ቊርባን
† ቡራኬ 17፡ ከዝማሬ ሱራፌል እስከ ጸሎተ ፈትቶ
† ቡራኬ 18፡ ቅድሳት ለቅዱሳን
† ቡራኬ 19: ነአኵቶ ለእግዚአብሔር ቅድሳቶ ነሢአነ
† ቡራኬ 20: አስተናጽሖ
† ቡራኬ 21: እትዉ በሰላም

• ማጠቃለያ
• መፍትሔ ቃላት (የቃላት መፍቻ)

መቅድም
ምክንያተ ጽሒፍ

አኰቴተ ቊርባን፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ መሠረት፣ ታሪካዊ እድገት እና ይዘት የተሰኘው መጽሐፌ የመጀመሪያ እትም ለንባብ ከበቃበት ኅዳር 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ስድስተኛው እትም እስከታተመበት ነሐሴ 2016 ዓ.ም. ድረስ በቃልም ሆነ በጽሑፍ የተለያዩ አስተያየቶች ደርሰውኛል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ሰፊ ጥናቶች ያደረጉ ሊቃውንት መጽሐፉ በተለይ ለካህናት፣ ለዲያቆናትና ለነገረ መለኮት (theology) ምሁራን ያለውን ጠቀሜታ አውስተውና ጠንካራ ጎኖቹን አድንቀው፣ በተሻለ መልኩ ሊቀርቡ ይገባቸዋል ያሏቸውን ነጥቦች ደግሞ በጽሑፍ እንዲደርሰኝ አድርገዋል፡፡ በርካታ ምእመናን አኰቴተ ቊርባን በቅዳሴ ውስጥ ያለውን የአምልኮ ውበት በማሳየት በአማርኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፋ ባለ መልኩ የተዘጋጀ መጽሐፍ በመሆኑ ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴያትና በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በየዘመናቱ የታዩትን የሥርዓተ አምልኮ ሂደቶች የሚያትቱት የመጽሐፉ ሁለተኛና ሦስተኛ ምዕራፎቸ ለካህናት ካልሆነ በስተቀር በቂ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሌላቸውን ሰዎች ትኩረት እንዳልሳቡ ሳይሸሽጉ ነግረውኛል፡፡ እንዲያውም መጽሐፉ ውስጥ በየገጹ የሚታዩትን የኅዳግ ማስታወሻዎች (footnotes) እንደ ትርፍ ነገር የቆጠራቸውና - ምንም እንኳን ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ሲደርስ ማስታወሻዎቹን ለማየት ቢገደድም - እነርሱን በማንበብ ጊዜ እንዳላጠፋ በግልጽ የነገረኝም ምእመን አጋጥሞኛል፡፡

መጠነኛ የንባብ ልምድ ያላቸው ሰዎች ዳጎስ ያሉ መጻሕፍትን ለማንበብ የሚያስችል ትዕግሥት እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡ ለቅዳሴ ካላቸው ፍቅር የተነሣ ከላይ የተጠቀሰውን መጽሐፍ ገዝተው ለማንበብ የሞከሩና “ቅዳሴ ምንድን ነው?” የሚል ርእስ የሰጠሁትን የመጽሐፉን የመጀመሪያ ምዕራፍና የቅዳሴን ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ከመጠነኛ ገላጻ ጋር የሚያስቃኘውን አራተኛውን ምዕራፍ ብቻ ያነበቡ ወገኖች እንዳሉም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ሲሳይ በገና የተባለ የቤተ ክርስቲያናችን አባል መጽሐፉ በቅዳሴ
ላይ ጥናት ማድረግ ለሚፈልጉ ሰዎች ያለውን ግብዐት አምኖበት፣ ነገር ግን በይዘቱ ትልቅ በመሆኑ (ከመግቢያውና መቅድሙ ውጪ 367 ገጾች አሉት) የንባብ ልምድ የሌላቸውን ምእመናን ትኩረት መሳብ ስላልቻለ፣ ምእመናን በቅዳሴ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያሳይና ቀለል ባለ መልኩ የተጻፈ ሁለተኛ መጽሐፍ እንዳዘጋጅ በfacebook የላከልኝ መልእክት ይህን መጽሐፍ እንድጽፍ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ ወንድማችን ሲሳይ የጻፈልኝ የfacebook ምክረ ሐሳብ ይህን ይመስላል፡-

ይህ መጽሐፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማያውቁት ለማስረዳት በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ለዓመታት በታመቀ እውቀት፣ በእምነትና በቁጭት የተጻፈ መጽሐፍ ሆኖ አገኘሁትና በፍቅር አነበብኩት። መጽሐፉ የጥናትና ምርምር መጽሐፍ በመሆኑ የንባቤ ትኩረት ቅዳሴው ላይ ብቻ ነበር፤ ከአቅሜ በላይ የሆኑትን መንፈሳዊና የታሪክ ጭብጦችን ጠልቄ ልመረምር አልሞከርኩም። መጽሐፉ በአብነትም በዘመናዊ ትምህርትም ተምረናል፣ አውቀናል ብለው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንንና ቅዳሴን ለሚያቃልሉ አላዋቂዎች ትዕቢታቸውን የሚያስተነፍስ ፍቱን መድኃኒት እንደሚሆን አስተውያለሁ። ቅዳሴን በዚህ ልክ ሰማያዊና ዓለም አቀፋዊ አገልግሎቱን፤ አስፈላጊነቱን፣ ጥቅሙን፣ ክብሩን፣ የቅዳሴ ዓላማና ግቡን አስረድቶ የጻፈ መጽሐፍ ከዚህ በፊት አላነበብኩም። ስለ ቅዳሴ ለማወቅ ይኽን መጽሐፍ ሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ሆኖ ሳለ፣ መጠኑ ትልቅ ስለሆነ በቤት ቁጭ ተብሎ እንጂ ለኪዳንም [ሆነ] ለቅዳሴ ሲሄዱ ይዘውት ሊንቀሳቀሱ ባለመቻሉ ቀዳሹም አስቀዳሹም በቀላሉ [ሊጠቀሙበት አልቻሉም]። ስለዚህ “አኰቴተ ቊርባን” መጠኑ ትልቅ ስለሆነ፣ የታተመው እንዳለ ባለው ይዘት ኅትመቱ ቀጥሎ፣ ዘወትር በቅዳሴ የሚሳተፉ ምእመናን በቀላሉ ከጸሎት መጽሐፋቸው ጋር ሊይዙት በሚችሉት መጠን ቀዳሹና አስቀዳሹ ሊያውቁት የሚገባውን ክፍል ስለቅዳሴ ለብቻ አውጥቶ በትንሹ መታተም ቢችል እጅግ በጣም ጥሩ ነው ብዬ ይህን የአደራ መልእክት አስተላልፋለሁ። (ትልቁ የቅዳሴው መጽሐፍ እያለ፤ ለምዕመናን [ለተሰጥዎ] መማሪያ ተብሎ በትንሹ በጸሎት መጽሐፍ መልክ እንደተዘጋጀው ዓይነት ማለት ነው)።

ብሌን ታከለ የቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል አባል ናት፡፡ የቅዳሴን ጣዕም ከልጅነቷ ጀምሮ የቀመሰችና ባደገችበት የሐዋሳ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ታላቅ የአገልግሎት ተሳትፎ የነበራት ልጅ ስለሆነች፣ አኰቴተ ቊርባን እጇ ውስጥ እንደገባ በደስታ አነበበችው፡፡ አቀራረቡን አስመልክቶ ግን ለየት ያለ አስተያየት ሰጠችኝ፡፡ “ቅዳሴን በትረካ መልኩ ያቀረበ መጽሐፍ መስሎኝ ነበር” አለች ብሌን፡፡ ይህን አስተያየት በርካታ ምእመናን ሊጋሩት እንደሚችሉ ተረዳሁ፡፡ ስለዚህ ይህ መጽሐፍ “ፍቅርተ ኢየሱስ” የተባለች፣ በጌታ የተወደደች፣ በደሙ እንደተዋጀች የምታውቅና የቅዳሴን ውበት እንድታይ በቅዱስ ቃሉ ትምህርት ዐይነ ልቡናዋ የበራላት ምእመን፣ ቅዳሴው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በጣዕመ ዜማው፣ ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በሚነበቡ ምንባባት፣ በቅዳሴው ጸሎትና ዑደት ሐሴት እያደረገች የቅዳሴው ተሳታፊ የምትሆንበትን ሂደት በዝርዝር ለማስረዳት ይሞክራል፡፡ ፍቅርተ ኢየሱስ ለቅዳሴ ካላት ፍቅር የተነሣ ዘወትር እሑድና በዐበይት በዓላት የቅዳሴ ተሳታፊ ስለምትሆን፣ ምእመናን ለዲያቆናቱና ለካህናቱ የሚሰጡትን የዜማ መልስ (ተሰጥዎ) በሚገባ ታውቃለች፤ መቅደሱ ላይ ያለውን የጌታ ስቅለት ሥዕል እያየች ዐይነ ልቡናዋን ወደ ቀራንዮ አቅንታ፣ ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ታዜማለች፡፡ በሥርዓተ አምልኮው ከሚከናወኑ ድርጊቶች መካከል ምሳሌያዊ ትርጉሙ ያልገባት ነገር ካለ ወይም በአብዛኛው ከሚቀደሱት ቅዳሴያት ለየት ያለ ቅዳሴ (ለምሳሌ ቅዳሴ ሠለስቱ ምእት፣ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፣ ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ ወዘተ.) ከተቀደሰ፣ የንስሐ አባትዋን ቀሲስ ፍቅረ መለኮትን ትጠይቃለች፡፡ እርሳቸውም መጽሐፈ ቅዳሴውን ይዘው የአማርኛውን ትርጉም እያስነበቡ ጥያቄዎቿን በሙሉ በዕርጋታና በዝርዝር ይመልሱላታል፡፡

ይህ መጽሐፍ ማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን አባል ስለ ቅዳሴ ሊያውቃቸው የሚገባቸውን መሠረታዊ ትምርህቶች ለማቅረብ ሙከራ አድርጓል፡፡ ትምህርተ ቅዳሴው የቀረበበትም መንገድ፣ የቅዳሴውን ሦስት ዋና ዋና ክፍልች በመከተልና ከየክፍሉ በተመረጡ አርእስት ላይ መጠነኛ ሐተታ (ገለጻ) በመስጠት ሲሆን፣ ፍቅርተ ኢየሱስ የተባለች ገጸ-ባሕርይ የቤተ ክርስቲያናችንን ምእመናን እንድትወክል ተደርጓል፡፡ በሦስቱ የቅዳሴ ክፍሎች ሥር የቀረቡ ትምህርቶችን በምዕራፍ ከመከፋፈል ይልቅ፣ “ቡራኬ 1፣ ቡራኬ 2 . . .” የሚል ስያሜን መርጫለሁ፡፡ ባጠቃላይ መጽሐፉ በሦስት ዐበይት ክፍሎችና በሃያ አንድ (21) ቡራኬያት የተከፈል ሲሆን፣ ትምህርታዊ ገላጻ የተሰጠባቸው ሃያ አንዱ ቡራኬያት፣ ሠራዒው ካህን በቅዳሴ ሰዓት የሚያከናውናቸውን ሃያ አንድ የአፍኣ (የውጭ) እና የውስጥ ቡራኬያትን ያስታውሱናል፡፡

በመጽሐፉ ውስጥ ለተጠቀሱ የግእዝ ቃላትና የሥርዓተ አምልኮ ስያሜያት (liturgical terminologies) መፍትሔ ቃላት (glossary) ተዘጋጅቷል፡፡ ምእመናንን ወክላ በዚህ መጽሐፍ የቅዳሴውን ሂደት በተመስጦ፣ አንዳንዴም በዕንባ፣ የምትከታተለው ፍቅርተ ኢየሱስ የቅዳሴ ጸበል ብቻ ጠጥታ ወደ ቤቷ የምትመለስ ሳትሆን፣ ጌታችን ኢየሱስ በቅዱስ ወንጌል “ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው” (ዮሐ. 6፡51) እንዳለ፣ ከኃጢአት በሽታ የምትፈወስበትን ኅብስተ ሕይወትና ጽዋዐ አኰቴት (ሥጋውና ደሙን) የምትቀበል ኦርቶዶክሳዊት ክርስቲያን ናት፡፡ ፍቅርተ ኢየሱስን በምናባቸው እየሳሉ ይህን መጽሐፍ የሚያነብቡ፣ ነገር ግን ከቅዱስ ቊርባን የራቁ ወይም ከተቀበሉ ዓመታትን ያስቆጠሩ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት በእውነተኛ ንስሐና በምክረ ካህን ተዘጋጅተው “ጸጋ ሆኖ የተሰጠንን ሥጋውንና ደሙን በእግዚአብሔር ጥበብ” እንደሚቀበሉ ተስፋ አደርጋለሁ - መልካም ንባብ፡፡

ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ (Ph.D.) ቶሮንቶ፣ ካናዳ
👍1
አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ
መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።
*********
የካቲት ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ/ም
+++++++++++++++++++
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።

ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ቄሰ ገበዞች ጋር ባደረገው ውይይትና ስምምነት መነሻነት የተለያዩ መመሪያዎች መተላለፋቸው ተገልጿል።

ከመመሪያዎች አንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከተለ መሆኑን ለሁሉም ገዳማትና አድባራት በተላከው የመመሪያ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ቅዳሴ የሁሉም ጸሎታት ማጠናቀቂያ ፣ ቀራንዮ ላይ ምንገኝበት፣ የበጉ ሠርግ ላይ የምንታደምበት፣የጌታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በአንድነት ለሓጢአት ሥርየት፣ ለነፍስ ሕይወት፣ ለሃይማኖት ጽንዐትና ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ይሆነን ዘንድ የምቀበልበት ታላቅ የጸሎት ሰዓት ነው።

በመሆኑም አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም ጎልጎታን ከሚያስረሱ ፣በረከትን ከሚያሳጡና ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ እንደተከለከለም ተገልጿል።

ይህንን መመሪያም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ መታዘዛቸውን በተጻፈ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው
👍32🕊1
ይህ ልዩ የወጣቶች መርሐግብር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ በሰፊው አጋሩልን።

ለመግባት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ።👉👉👉https://us02web.zoom.us/j/85438850192?pwd=AWIYSXtOlzahCTkDbpRot8A8irQNaM.1
ሌላ ሰሞነኛ ጉዳይ

"ገድላት ያስፈልጋሉ አያስፈልጉም አንልም፤ ነገር ግን ከታሪካቸው መርጠንና በራሳችን አእምሮ መዝነን ነው የምንቀበላቸው"

is another version of

"ገድላትን የመቀበል ግዴታ የለባችሁም"!

and the consequence is

"ሳንመራመርና ሳንፈላሰፍ የምንቀበለው መጽሐፍ ቅዱስ እያለ ትክክል ይሆን አይሆን እያልን የምንወዛገብበት ገድል ምን ይሠራል?"

and so the final conclusion is

"ገድላት አያስፈልጉም"!

➺ ይህንን አስልተው የሚጫወቱ አሉ። ሳያውቁ የእነዚህ ባለ ስሌቶች ተገዢዎች አሉ። የሁለቱም ውጤት አንድ ነው።

"አቀፈም አዘለም ያው ተሸከመ ነው"!

(በነገራችን ላይ በራሳችን ማስተዋል የምንደገፍና በራሳችን ሚጢጢ አእምሮ የምንመዝን ከሆነ መጽሐፍ ቅዱሱንም መንቀፋችን አይቀርም! ወይም ገድላትን እንድንቀበል የግድ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ጋር አንድ ዓይነት ገድልና ተአምራት ብቻ ይዘው መገኘት የለባቸውም!)

Credit to Moges Kahssay
👍43
ChatGPT እስኪ ስለዚህ ነገር አብራሪልኝ ብዬ ጠየኳትኝ የሚያስገርም መልስ መልሳልኛለች ላጋራችሁ
1
Here’s a summary and analysis of the requested text:

Summary

The passage discusses the imagery of Adam and Eve as a parallel to the Virgin Mary's conception and birth of Christ, as interpreted by Jacob of Serugh. The last part of page 160 and the first two paragraphs of page 161 emphasize the idea that Eve was created from Adam’s side without causing corruption to his body. This serves as a typological reference to Christ’s birth from Mary, which also did not alter her virginity.

Jacob of Serugh presents a theological analogy: just as Adam generated Eve without a marital union, Mary, through the Holy Spirit, conceived and gave birth to Jesus without human intercourse. The purity found in Adam is mirrored in Mary, who, by divine intervention, became the mother of Christ without any lustful impulse. Furthermore, Adam's role in generating Eve without union is seen as a foreshadowing of the Virgin Birth, reinforcing the idea of divine purity and spiritual conception.

Analysis

This passage is a theological reflection on virginity and divine intervention in birth, a common theme in early Christian thought. Jacob of Serugh employs typology, a method of biblical interpretation that sees Old Testament events as prefiguring New Testament realities. Here, Adam symbolizes purity before sin, and Eve’s creation without sexual union serves as a precedent for Mary’s virginal conception.

The passage reinforces the notion of divine agency in creation and birth, portraying both Eve’s formation and Christ’s birth as acts of divine will rather than natural reproduction. This argument upholds the doctrine of Mary’s perpetual virginity and aligns with the broader Christian tradition that views Christ’s birth as a miraculous fulfillment of divine prophecy.

Would you like a more in-depth theological analysis?

አዎ አልኳት

In-Depth Theological Analysis

Jacob of Serugh, a 5th-6th century Syriac poet-theologian, uses typology to connect the Old Testament creation narrative with the New Testament doctrine of the Virgin Birth. His interpretation is deeply rooted in patristic theology, where Adam and Eve serve as foreshadows of Christ and Mary. This method aligns with early Christian exegesis, particularly in the Syriac tradition, which often drew analogies between Genesis and Christ’s redemptive work.

1. Adam as a Type of Christ, Eve as a Type of Mary

Jacob presents Adam as a prefiguration of Christ and Eve as a parallel to Mary. The creation of Eve from Adam’s side without marital union is seen as a precursor to Christ’s birth from Mary without human intercourse. This typological reading suggests that just as Eve was formed without the corruption of natural generation, so too was Christ born without disrupting Mary’s virginity. This reinforces the theological claim that Christ’s birth was unique—both fully divine and fully human—while preserving Mary’s purity.

2. The Role of the Holy Spirit in Birth and Creation

The passage emphasizes the role of the Holy Spirit in both the creation of Eve and the conception of Christ. Jacob describes how the Holy Spirit "blew on Adam’s face and generated Eve," mirroring how Mary "received and gave birth to a Son" by the power of the Spirit. This poetic parallel strengthens the idea that divine breath (ruach, meaning "spirit" in Hebrew) is the creative force behind both events. By linking these two moments, Jacob highlights the continuity between the Old and New Covenants, showing that divine intervention operates beyond natural reproductive processes.

3. Virginity and the Absence of Lust
👍1
Jacob contrasts the purity of Adam before sin with the purity of Mary, emphasizing that both conceptions—Eve from Adam and Jesus from Mary—occurred without "impulse of lust." This reflects early Christian concerns about original sin and the fallen nature of human sexuality. Theologians like Augustine argued that sexual reproduction, while not inherently sinful, was tainted by concupiscence (disordered desire) after the Fall. By emphasizing that both Eve and Christ came into the world through divine rather than sexual means, Jacob reinforces Mary’s role as the new Eve—one who, unlike the first, participates in redemption rather than the Fall.

4. Adam’s Role as "Father" of Life and Christ as the Fountain of Life

The final lines describe Adam as generating "the mother of life," a reference to Eve, and foreshadowing Christ, who is "the fountain of life." This points to a theological progression: Adam's act of bringing forth Eve prefigures Christ’s role as the ultimate source of eternal life. While Adam’s role was biological and symbolic, Christ’s role is salvific, bringing spiritual rebirth to humanity. In this way, Jacob frames Christ as the fulfillment of Adam’s incomplete role—where Adam failed, Christ succeeds in bringing true and eternal life.

Conclusion

Jacob of Serugh’s interpretation is rich with Syriac theological themes: the role of divine breath (Spirit) in creation, typological connections between the Old and New Testaments, and the purity of virginity as a marker of divine intervention. His imagery not only reinforces the doctrine of the Virgin Birth but also elevates Mary’s status within salvation history. She is not merely a passive vessel but an active participant in God's redemptive plan, mirroring Eve’s role while simultaneously reversing her transgression.

This theological perspective aligns with broader patristic thought but is especially characteristic of the Syriac tradition, which often emphasized poetic and mystical interpretations of biblical events. Jacob’s approach blends biblical exegesis with theological reflection, offering a profound meditation on divine purity, the role of the Spirit, and the transformative power of Christ’s birth.

Would you like further elaboration on any of these points?

አይበቃም?

አይበቃም?
ቅዱስ አትናቴዎስ ስለ ጾም

ስለ ጾም የሰጠው ትምህርት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ ጾምን እንደ መንፈሳዊ መሳሪያ በመቁጠር በርካታ ትምህርቶችን አስተላልፏል።

ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
• የጾም ዓላማ:

• ቅዱስ አትናቴዎስ ጾም ከምግብ መከልከል ብቻ ሳይሆን ከኃጢአት መራቅና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንደሆነ አስተምሯል።
• ጾም የሥጋን ፈቃድ በመግዛት መንፈሳዊ ንጽሕናን እንደሚያጎናጽፍ አጽንኦት ሰጥቷል።
• በተጨማሪም ጾም የንስሐ ጊዜ በመሆኑ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት እንድናድስ ይረዳናል ብሏል።
• የጾም አስፈላጊነት:
• ቅዱስ አትናቴዎስ ጾም የክርስቲያናዊ ሕይወት አንዱ አካል እንደሆነና ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንደጾመ አስተምሯል።
• ጾም የሰይጣንን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል ኃይል እንደሚሰጥ ገልጿል።
• ጾም ለምህረት እንደሚያበቃም አስተምሮአል።
• የጾም አፈጻጸም:
• ቅዱስ አትናቴዎስ ጾም በጸሎት፣ በምጽዋትና በንሰሐ መታጀብ እንዳለበት አሳስቧል።

• ጾምን በሥርዓት እንድንጾም አስተምሮአል።

ቅዱስ አትናቴዎስ ጾም መንፈሳዊ እድገትን ለማምጣት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከርና ከኃጢአት ለመራቅ የሚረዳ አስፈላጊ መሳሪያ እንደሆነ አስተምሯናል ።
👍1
2025/08/30 14:52:22
Back to Top
HTML Embed Code: