tgoop.com/uthmanovich/2989
Last Update:
ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ እየተፈናጀሉ መፈናጀል ብቻ ሳይሆን ባይብል ውስጥ እኮ እግዚአብሔር እራሱ ለምጻሙን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ በሬሳም የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ አዟቸዋል፦
ዘኍልቍ 5፥1-4 *"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ በሬሳም የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤ ወንዱንና ሴቱን አውጡ፤ እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈሩ አውጡአቸው። የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፥ ከሰፈሩ አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ"*።
"ሰፈር"camp" ሁሉም ሰው የማይገባበት ሥፍራ ነው። ከላይ የተዘረዘሩት ሰዎች የሚወጡበት ምክንያት ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ነው፥ "ከሰፈሩ አወጡአቸው" የሚለው ይሰመርበት። በአዲስ ኪዳንም ቢሆን ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ከሆነ ከእርሱ ጋር ምግብ መብላት የተከለከ ነው፥ ከዚያም ባሻገር፦ "አውጡት" የሚል ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 5፥11-13 *"አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት"*።
የማትገቡበት ቦታ የማትረግጡት ዋልታ እንደሌለ ሁሉ እኛም ባይብል ላይ ገብተን አሳብን ረብጣ በሆነ አሳብ ማረቃችንና ማርቀቃችን አይቀርም። የወታደር ሰፈር"cantonment" ለተለየ ዓላማ ከወታደር ውጪ ማንም አይገባም፥ የገባም እንዲወጣ ይደረጋል፥ ያ ማለት ሰውን ማግለል እንዳልሆነ እና እዛ ሰፈር ለመግባት መስፈርቱ ወታደር መሆን እንደሆነ ሁሉ መካህ እና መዲናህ ውስጥ ለመኖር መስፈርቱ ሙሥሊም መሆን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY 🎙uthmanovich የንፅፅር channal !!!🎓
Share with your friend now:
tgoop.com/uthmanovich/2989