tgoop.com/uthmanovich/2992
Last Update:
ኡማህ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
16፥36 *”በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍۢ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّٰغُوت
“ኡማህ” أُمَّة የሚለው ቃል “አመ” أَمَّمَ ማለትም “በዛ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሕዝብ” ወይም “ብዙኃን” ማለት ነው። “ኡመም” أُمَم የኡማህ ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕዝቦች” ማለት ነው። ለምሳሌ አምላካችን አሏህ በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ” በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልኳል፦
16፥36 *”በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍۢ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّٰغُوت
እዚህ አንቀጽ ላይ "ሕዝብ" ለሚለው የገባው ቃል "ኡማህ" أُمَّة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በባይብልም ቢሆን "ሕዝብ" ለሚለው የገባው የዐረማይኩ እና የዕብራይስጡ ቃል "ኡማህ" אֻמָּה ነው፦
ዳንኤል 3፥29 *"እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገን እና "ሕዝብ" በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ"*። ומני שים טעם די כל־עם אמה ולשן די־יאמר [שלה כ] (שלו ק) על אלההון די־שדרך מישך ועבד נגוא הדמין יתעבד וביתה נולי ישתוה כל־קבל די לא איתי אלה אחרן די־יכל להצלה כדנה׃
እዚህ አንቀጽ ላይ "ሕዝብ" ለሚለው የገባው ቃል "ኡማህ" אֻמָּה መሆኑም ልብ አድርግ! የሕዝብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አሕዛብ" ሲሆን "ሕዝቦች" ማለት ነው። ሌላም ጥቅስ ላይ ሳይቀር "አሕዛብ" ወይም "ሕዝቦች" ለሚለው የገባው ቃል "ኡማህ" אֻמַּה ሲሆን ብዙ ቁጥሩ ደግሞ "ኡሚም" אֻמִּֽים ነው፦
መዝሙር 117፥1 *"አሕዛብ ሁላችሁ ያህዌህን አመስግኑት! "ወገኖችም" ሁሉ ያመስግኑት"*። הַֽלְל֣וּ אֶת־יְ֭הוָה כָּל־גֹּויִ֑ם בְּח֗וּהוּ כָּל־הָאֻמִּֽים
ስለዚህ "ኡማህ" ማለት "ኢሥላማዊ ሕዝብ" ማለት ነው፥ "ኦሮሙማ" ማለት "የኦሮሞ ኢሥላማዊ ሕዝብ" ማለት ነው" ላላችሁን የኦርቶ-ዐማራህ የፓለቲከኛ ነጋዴዎች ከላይ ያለውን ቃል በዛ ቀመር እና ስሌት ተርጉሙት እና መቀመቅ ውስጥ እንደምትገቡ አልጠራጠርም።
"ኦሮሞ" Oromo በሚለው መድረሻ ቅጥያ ቃል ላይ "ኦሮሞነት" ብለን ባሕርይን ለማመልከል ስንፈልግ "ኦሮሙማ" Oromummaa ብለን እንጠቀማል፥ ለምሳሌ፦
፨"ቢሊሰ" Bilisa ማለት "ነጻ" ማለት ሲሆን "ነጻነት" ብለን ባሕርይ ለማመልከት ደግሞ "ቢሊሱማ" Bilisummaa እንላለን፣
፨"ቶኮ" Tokko ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን "አንድነት" ብለን ባሕርይ ለማመልከት ደግሞ "ቶኩማ" Tokkummaa እንላለን፣
፨"ኢትዮጵያ" Itiyoopiyaa ብለን "ኢትዮጵያዊነት" ብለን ባሕርይ ለማመልከት ደግሞ "ኢትዮጵያዉማ" Itiyoopiyaawummaa እንላለን።
እዚህ ድረስ ከተግባባን እስቲ ይህንን ጠባብ ሙግት በቋንቋ ሙግት አፈታት እንመልከት፦
"ዐማሐራህ" ማለት የሁለት የዕብራይስጥ ቃላት ውቅር ነው፥ "አማ" "ኡማ" ማለት "ሕዝብ" ማለት ሲሆን "ሐራማ" "ሐርማ" ማለት "ተራራ" ማለት ነው። በጥቅሉ "በተራራ ላይ የሚኖር ሕዝብ" ማለት ነው፥ በኦርቶ-ዐማራህ ትርጉም "ዐማ" ማለት ሃይማኖት ሲሆን "ሐራማ" ማለት ዘር ማለት ነው" በማለት ዐማራ ማለት የዘር እና የሃይማኖት ውሕደት እንበል? እንደውም "መስከረም" ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "መስክ" ማለት "ሜዳ" ማለት ሲሆን "አረም" ማለት "ያልታረመ" ማለት ነው። በጥቅሉ "መስከረም" ማለት "የመስክ አረም" ማለት ነው፥ "ያልታረምሽ የሜዳ አረም ወይም በዬኔታ ሚዲያ ላይ ያልታረመ ቃላት የምትዘራ" እንበላት? ያስኬዳል? እንዲህ መቦተረፍ ይቻላል፥ ቅሉና ጥቅሉ ግን ቅጥፈት መጋለጡ አይቀርም። እረ በመጠበብ ዘመን አንጥበብ!
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY 🎙uthmanovich የንፅፅር channal !!!🎓
Share with your friend now:
tgoop.com/uthmanovich/2992