tgoop.com/uthmanovich/3012
Last Update:
የሴት ደረጃ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ
“ፈድል” فَضْل የሚለው ቃል “ፈዶለ” فَضَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስጦታ” “ችሮታ” “ጸጋ”Bounty” ማለት ነው፥ ሴትነት እና ወንድነት በተፈጥሮ ከአሏህ የተሰጠን ጸጋ ነው፦
4፥32 *”አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በእርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ! ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፡፡ وَلَا تَتَمَنَّوْا مَا فَضَّلَ اللَّهُ بِهِ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ لِّلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبُوا ۖ وَلِلنِّسَاءِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبْنَ
እዚህ አንቀጽ ላይ “ያበለጠ” ለሚለው ቃል የገባው “ፈዶለ” فَضَّلَ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል! ወንድነት ለወንድ የተሰጠ ጸጋ ነው፥ ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው። ሴትነት ለሴት የተሰጠ ጸጋ ነው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው። ለወንድ የተሰጠውን ጸጋ ሴት መመኘት የለባትም! ለሴት የተሰጠ ጸጋ ወንድ መመኘት የለበትም፥ ወንድ በሴት ላይ ሴት በወንድ ላይ የሚበላለጡት ጸጋ አለ እንጂ ወንድ ሴት አይደለም እንዲሁ ሴት ወንድ አይደለችም፦
3፥36 “ወንድም እንደ ሴት አይደለም”፡፡ وَلَيْسَ الذَّكَرُ كَالْأُنثَىٰ
አንድ ተባእት አምኖ መልካም ከሠራ መልካም ኑሮን በሚኖርበት መጠን አንድ እንስትም አምና መልካም ከሠራች መልካም ኑሮን ትኖራለች፦
16፥97 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً
አንድ ተባእት አምኖ መልካም ከሠራ ጀነት እንደሚገባ ሁሉ አንድ እንስትም አምና መልካም ከሠራች ጀነት ትገባለች፦
4፥124 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ
40፥40 “እርሱ ምእመን ኾኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ”፡፡ وَمَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ
9፥72 “አላህ ምእምናንን እና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል”፡፡ وَعَدَ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ ۚ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ أَكْبَرُ
ወንድ አማኞች “ሙእሚኒን” مُؤْمِنِين ሲባሉ ሴት አማኞች “ሙእሚናት” مُؤْمِنَات ይባላሉ፥ በጀነት ውስጥ ወንድ አማኞች እና ሴት አማኞችም የሚፈልጉት ነገር ሁሉ አለላቸው፦
25፥16 ለእነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ኾነው የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህም ተስፋ ከጌታህ ተለማኝ ተስፋ ነው፡፡ لَّهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ خَالِدِينَ ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ وَعْدًا مَّسْئُولًا
39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ
43፥71 “በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት እና ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አለ፥ እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ፡፡ وَفِيهَا مَا تَشْتَهِيهِ الْأَنفُسُ وَتَلَذُّ الْأَعْيُنُ ۖ وَأَنتُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
41፥31 ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አለላችሁ፡፡ ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምትፈልጉት ሁሉ አለላችሁ”፡፡ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَشْتَهِي أَنفُسُكُمْ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ
16፥31 “ለእነርሱም በወስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል”፡፡ لَهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْزِي اللَّهُ الْمُتَّقِينَ
BY 🎙uthmanovich የንፅፅር channal !!!🎓
Share with your friend now:
tgoop.com/uthmanovich/3012