tgoop.com/uthmanovich/3013
Last Update:
“ተቅዋእ” تَقْوَى ማለት “አሏህ መፍራት” ማለት ሲሆን አሏህን የሚፈሩ ወንድ እና ሴት “ሙተቂን” مُتَّقِين ይባላሉ፥ ለሙተቂን በጀነት ውስጥ ከአሏህ የኾነ ውዴታ ጥንዶች አላቸው፦
3፥15 «ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው፡፡ እርሱም፦ «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ አዝዋጅ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው» قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ ۚ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ
“ዘውጅ” زَوْج የሚለው ቃል “ዘወጀ” زَوَّجَ ማለትም “ተጠናዳ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጥንድ” “ባል” “ሚስት” ማለት ነው፥ 58፥1 ላይ “ባልዋ” ለሚለው የገባው ቃል “ዘውጂሃ” زَوْجِهَا ሲሆን 7፥19 ላይ “ሚስትህ” ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ “ዘውጁከ” َزَوْجُكَ ነው። የዘውጅ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አዝዋጅ” أَزْوَاج ሲሆን “ጥንዶች” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ በግስ መደብ “ዘወጅናሁም” زَوَّجْنَاهُم ማለትም “እናጠናዳቸዋለን” ብሎ ቃል ገብቷል፦
44፥54 ነገሩ እንደዚሁ ነው፥ ሁር ዒን እናጠናዳቸዋለን፡፡ كَذَٰلِكَ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ
“አሕወር” أَحْوَر ማለት “ውብ” ማለት ሲሆን ተባታይ መደብ ነው፥ “ሐውራእ” حَوْرَاء ማለት ደግሞ “ውቢት” ማለት ሲሆን አንስታይ መደብ ነው። “ሑር” حُور ማለት የሁለቱም ጾታ ብዜት ነው፥ “ዒን” عِين ማለት “ዓይናማ” ” ማለት ነው። “ሑረል ዒን” حُور العِين ማለት በጥቅሉ “ውብ ዓይናማ” ማለት ነው። በጀነት “ነፍሶች የሚከጅሉት እና ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አለ” እንደተባለው “ሑረል ዒን” አምላካችን አሏህ ለወንድ እና ለሴት ሙተቂን ባሮቹ ያዘጋቻቸው ናቸው፥ አምላካችን አሏህ ጥንድን ያጠናዳው ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሳችን እና ከማናውቀው ነገር ነው፦
36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሳቸውም እና “ከማያውቁትም ነገር" ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي خَلَقَ الْأَزْوَاجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنبِتُ الْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 36፥36 "ከዚያም አለ፦ "ያ ምድር ከምታበቅለው ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው" ማለት ሰብልን፣ ፍራፍሬን እና አታክልትን ማለት ነው። "ከራሳቸውም" ማለት ከወንድ እና ከሴት አደረገላቸው ማለት ነው። "ከማያውቁትም ነገር" ማለት የማይታወቁ የተለያዩ ፍጥረት ማለት ነው።
ثم قال : ( سبحان الذي خلق الأزواج كلها مما تنبت الأرض ) أي : من زروع وثمار ونبات . ( ومن أنفسهم ) فجعلهم ذكرا وأنثى ، ( ومما لا يعلمون ) أي : من مخلوقات شتى لا يعرفونها.
፨ አንደኛ "ምድር ከምታበቅለው" ማለት ከምድር ውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው፦
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ
፨ ሁለተኛ "ከራሳቸውም" ማለት ከራሳችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ ያደረገ ነው፦
30፥21 ለእናንተም ከራሳችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً
፨ ሦስተኛ "ከማያውቁትም ነገር" ማለት ሑረል ዒን አዲስ ፍጥረት አድርጎ ለሙተቂን ከዓይኖች መርጊያ የተደበቀላቸውን ጸጋ ሲሆን ይህንን ጸጋ አሁን ላይ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም፥ በጀነት ውስጥ ያለው ጸጋ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልብ ውልብ ብሎ የማያውቅ ነው፦
56፥35 እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን ለእነርሱ ፈጠርናቸው፡፡ إِنَّا أَنشَأْنَاهُنَّ إِنشَاءً
32፥17 ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 302
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የላቀው አሏህም እንዲህ አለ፦ “እኔ ለደጋግ ባሮቼ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልብ ውልብ ብሎ የማያውቅ ጸጋን አዘጋጅቻለው”። ከዚያም እርሳቸው፦ “ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም” የሚለውን አንቀጽ አነበቡ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم ” يَقُولُ اللَّهُ تَعَالَى أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ، ذُخْرًا، بَلْهَ مَا أُطْلِعْتُمْ عَلَيْهِ ”. ثُمَّ قَرَأَ {فَلاَ تَعْلَمُ نَفْسٌ مَا أُخْفِيَ لَهُمْ مِنْ قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ}
በተረፈ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 238 ላይ ወይም ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 46 ላይ አሊያም ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 38, ሐዲስ 2760 ላይ “ሰባ ሁለት አዝዋጅ” የሚለውን ሙሐዲስ ሸይኽ አል-አልባኒይ ረሒመሁል ሏህ “ደረጃቸው ዶዒፍ ናቸው” ብለዋቸዋል፥ ዶዒፍ ደግሞ መቅቡል ሳይሆን መርዱድ ነው።
አሏህ በጀነት ያዘጋጀልንን ጸጋ ይወፍቀን! አሚን።
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY 🎙uthmanovich የንፅፅር channal !!!🎓
❌Photos not found?❌Click here to update cache.
Share with your friend now:
tgoop.com/uthmanovich/3013