tgoop.com/uthmanovich/3023
Last Update:
በእንቅልፍ ልብ፣ በዕብደት እና በእንጭጭነት የሚደረግ ሥራ መላእክት አይመዘግቡትም። አንድ ሕጻን ለዐቅመ-አደም ከደረሰ የሰው ቤት ዘው ብሎ አይገባም፥ ከዚያ ይልቅ አንኳክቶ ያስፈቅዳል፦
24፥59 *"ከእናንተም ሕፃናቶቹ አቅመ አዳምን በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ"*፡፡ وَإِذَا بَلَغَ الْأَطْفَالُ مِنكُمُ الْحُلُمَ فَلْيَسْتَأْذِنُوا كَمَا اسْتَأْذَنَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ
አሁን እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢዛ" إِذَا የሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ የዐቅመ-ጋብቻ ጊዜ አመላካች ነው፥ ይህንን ዐቅመ-ጋብቻ ለማመልከት "በለገ" بَلَغَ የሚል የግስ መደብ ይጠቀማል። አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ የመድረሷ የመጀመሪያው እና ዐቢይ ምልክት አድሬን-አርክ"adrenarche" አካሏ ለተራክቦ ዝግጁ ሲሆን እንዲሁ ጡቷ ሲያጎጠጉጥ ቴል-አርክ"thelarche" እና ብብቷና ብልቷ አካባቢ ጸጉር መብቀል ፑብ-አርክ"Pubarche" ሲጀምር የምታመነጨው ፈሳሽ"Vaginal lubrication" እንጂ የወር አበባ አይደለም፥ የወር አበባ ማየት አንዲት ሴት ለዐቅመ-ሐዋህ መድረሷን ከሚያሳዩ ሁለተኛ እና ንዑስ ምልክት ዕንቁላል ማምረት ጎናድ-አርክ"gonadarche" እንዲሁ የወር አበባ ደም ሜን-አርክ"menarche" ነው። አንዲት ሴት ስታርጥ የወር አበባ ይቋረጣል፥ ያኔ የምታመነጨው ፈሳሽ ያለ የወር አበባ ተራክቦ ማድረግ ትችላለች። ምክንያቱም ተራክቦ ለማድረግ የወር አበባ ብቻውን መስፈት አይደለም፥ የወር አበባ ለፅንስ እንጂ ለተራክቦ መስፈት አይደለም፦
65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው"*፡፡ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ
“ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው። "ዐደፍ" ለሚለው የገባው ቃል "መሒድ" مَحِيض ሲሆን "የወር አበባ" ማለት ነው። አንድ ወንድ ከዐደፍ ያቋረጠች ማለትም ያረጠች ሴት ለመፍታት ምናልባት አርጣለች ተብሎ እግዝና ስለሚከሰት የሦስት ወር ጊዜ ይኖራታል። አንዲት ሴት ልጅ ለዐቅመ-ሐዋህ ስደርስ ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግና የሚያጣብቅ ቀለም አልባ እና ሽታ አልባ ቀጭን ፈሳሽ"nocturnal emission" አላት፥ ነገር ግን ይህ ፈሳሽ ኖሮ የወር አበባዋ ሳይመጣ ብዙ ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ይህንን የወር አበባ ያላዩ ሴቶች መሃል ላይ እንቁላል ማምረት ችለው እርግዝና ሊከሰት ስለሚችል ሦስት ወር ባል የማይፈታበት ጊዜ አለ፦
2፥235 *የተጻፈውም ዒዳህ ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ አሳብ አታድርጉ፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ"*፡፡ وَلَا تَعْزِمُوا۟ عُقْدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْكِتَٰبُ أَجَلَهُۥ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ فَٱحْذَرُوهُ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌۭ
እንግዲህ ዐቅመ-ሐዋህ ጅማሬው አካላዊ ሽግግር"physical transition" የሆኑት ጡቷ ማጎጥጎጥ፣ ብብትና ብልት አካባቢ ጸጉር ማብቀል፣ የተራክቦ ፈሳሽ ማመንጨት ሲሆን ቀጣዩ የእንቁላል እድገት"ovarian development" ልጅ ለመፅነስ መደላድል ነው፥ እንቁላሉ የወንድ የዘር ሕዋስ ካላገኘ የወር አበባ ሆኖ ይወጣል። ይህንን በቅጡ ያልተረዱ ሚሽነሪዎች ዐይናቸውን በማንሸዋረር "የወር አበባ ያላየች ሴት" የሚለውን "ለዐቅመ-ሐዋህ ያልደረሰች" ብለው በማውረግረግ ኢሥላምን ሊዘልፉ ይፈልጋሉ፥ ይህ የደፈረሰ መረዳት ከላይ ያለውን ተስተምህሮት ጥልልና ጥንፍፍ አድርጎ ካለማየት የመጣ የተሳከረ መረዳት ነው። በኢሥላም ምንም ነገር መጉዳት አይፈቀድም፥ ጉዳትም ካለ በቂሷስ ይፈረዳል እንጂ ጉዳት አይመለስም፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 34
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ *"መጉዳት የለም፥ ጉዳትንም መመለስ የለም"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ لاَ ضَرَرَ وَلاَ ضِرَارَ ” .
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY 🎙uthmanovich የንፅፅር channal !!!🎓
Share with your friend now:
tgoop.com/uthmanovich/3023