tgoop.com/wsumsj/882
Last Update:
✅በረመዷን ወቅት ቁርአን መቅራት
شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ. البقرة: ١٨٥
ረመዷን ቁርአን ለሰው ልጆች እንደ መመረያ፤ (በእውነትና በውሸት መካከል) መለያ እና ግልፅ መመሪያና ማስረጃ ሆኖ የወረደበት ወር ነው። {አል-ቁርአን 2:185}
ሙሉ የረመዷን ወር ከሌሎች ኢባዳዎች ጋር ቁርአን በመቅራት ልናሳልፈው ይገባል። አሏህ በሱረቱ ሉቅማን አንቀፅ 3 ላይ እንደገለፀው ቁርአን “ለመልካም ሰሪዎች መመሪያና እዝነት ነው።” ቁርአን ህይወት ፣ ሸፈአ ፣ ደስታ ፣ ምንዳ ፣ እዝነት ፣ መድሃኒት ፣ መለኮዊ አስተምህሮት ፣ ከህግም በላይ ህግ የሆነ ዘላለማዊ ጥበብ ነው።
በቡኻሪ በተዘገበ ሐዲስ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ቁርአን አንብቡ በእርግጥ በፍርዱ ቀን ሸፈአ(አማላጅ) ይሆንላችኋልና ብለዋል።
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በመጨረሻ አመታቸው ረመዷን ውስጥ ሁለት ጊዜ አክትመዋል። እኛ ሙስሊሞችም የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ በመከተል በረመዷን ወቅት ቢያንስ አንድ ጊዜ ማኽተም ይኖርብናል።
ይሁንእንጅ በአሁኑ ወቅት አብዛሃኛዎቻችን ቁርአን የምንቀራው በረመዷን ብቻ እየሆነ ነው። ይባስ ብሎ ለማክተም የሚደረግው ጥረት የተራዊህ ወይም የተሃጁድ ሶላት ላይ ነው። በተራዊህ ሶላት ለማኽተም ሩጫ ነው። በእርግጥ ይህ ተግባር የቁርአን አስተህሮትን ይቃረናል። ምክኒያቱም አሏሁ አዘወጀል “ቁርአንን በዝግታ አንብብ” ብሏል (73:4)።
ኢብን ከሲር ይህን የቁአን አንቀፅ ሲያብራሩ ይህ ማለት ቁርአንን ለመረዳትና ለማስተንተን ይረዳህ ዘንድ ቀስ ብለህ ቅራ ማለት ነው። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ይቀሩ የነበረውም እንዲህ ነው ሲሉ አብራርተዋል። ሆኖም ቁርአን ስንቀራ ወይም በረመዷን ለማኽተም ስንጥር ይህን የቁርአን አያ ተከትለን መሆን ይኖርበታል። የበለጠ ወደ አሏህ ለመቅረብ ስንቀራ እያስተነተን እና ተረድተነው ይሁን። ቁርአን ማንበብ የማንችል ሰዎች እያንዳንዷን ቀን በሲዲ የተቀረፀ ቁርአን ለማዳመጥ እንሞክር። ወይም ደግሞ በአፍ መፍቻ ቋንቋችን የተተረጎመ ቁርአን በማንበብ ማሳለፍ ይኖርብናል።
https://www.tgoop.com/sunah123
BY 📚በወ.ሶ.ዩ.ሙ.ተ.ጀ የሚሰጡ ቂርኣቶች የሚለቀቁበት ቻናል📚

Share with your friend now:
tgoop.com/wsumsj/882