tgoop.com/yasin_nuru/5115
Last Update:
አስራሚ እውነተኛ ታሪክ
የታሪኩ ረእስ☘ የተቅዋ ጠቀሜታ☘
አንድ እውቀት ፈላጊ ተማሪ እና እርሱን የሚያስተምሩት አንድ አሊም ነበሩ። እኝህ አሊም ከለታት አንድ ቀን ለዚህ ተማሪና ለጎደኞቹ የሚከተለውን ምክር መከሯቸው ከሰው ዘንድ ለማኝ ከጃይ እንዳትሆኑ። አሊም የሆነ ሰው እሲ ስጡኝ ብሎ እጁን ወደሰው የሚዘረጋ ከሆነ ምንም ኸይር አያገኝም። ለራሱም ለድኑም ውርደት ነው የሚከናነበው። ስለዚህ እናነተ ወዳባቶቻችሁ ሂዱና አባቶቻችሁ የሚሰሩትን ስራ ስሩ ወይም አግዞቸው። ታዳ በምትሰሩት ስራ ሁሉ አላህን ፍሩ። ከዚህ ቡሀላ ተማሪወቹን ወደ የጉዳያቸው አሰናበቱአቸው።
ይህ ወጣት ተማሪ ወደ እናቱ ሄደና አባቴ የሚሰራው ምን አይነት ስራ ነበር ብሎ ጠየቃት። እናቲቱም የአባቱን ስራ ለመንገር በጣም ተቸገረች። እንደገና ቡሀላ አባት ወደ አኼራ ሂዲአል የእርሱ ስራ ላንተ ምን ያደርግልሀል አለችው። ልጁ ካልነገርሽኝ ብሎ አስጨነቃት። ጥያቄ ሲያበዛባት አባትህ ሌባ ነበር አለችው።
ልጅየውም ሸይኻችን አባታችን የሚሰራውን ስራ እንድንሰራ ነገር ግን አላህ መፍራት እንዳለብን መክረውናል አላት። እናቲቱም ምን ማለትህ ነው? እየሰረክ እንዴት ነው አላህን የምትፈራው? ስትል የግርምት ጥያቄዋን ጠየቀችው። እናትና ልጅ በሀሳብ ሳይግባቡ ተለያዩ። ልጁ ግን ወደ አንድ ቦታ ሂዶ የአሰራረቅ ዘደወችን ተማር።
በሌብነት ስልቶች ከተካነ ቡሀላ ትምህርቱንም የሸህየውን ምክርም ተግባራዊ ለማድረግ ወሰነ። የኢንሻን ሶላት ሰግዶ ሰው እስኪተኘ ድረስ አድፍጦ ጠበቀ። ከዚያም ከቤቱ ወጣ በቅድሚያ ወደአንድ ጎረቢት ቤት ወስጥ ገብቶ ለመስረቅ ነበር ያሰበው። ነገር ግን የሸህየውን አላህ ፍሩ ተግሳጽ አስታወሰ ጎረቢትን ማስቸገር አላህ ከመፍራት አይደለም አለና ይህንን ቤት አልፎ ወደሌላ ቤት ተሻገረ። ይህ ቤት ደግሞ የየቲሞች ነው ለነፍሱም ይህ ቤት የየቲሞች ቤት ነው። አላህ ደግሞ የየቲሞችን ገንዘብ መብላት እርም ( ሀራም) አድርጎታል አለ።
ይህንኛውንም ቤት ትቶ ወደቀጣዩ ቤት አለፈ። እንድህ እንድህ እያለ ወደ አንድ ሀብታም ነጋደ ቤት ደረሰ ቤቱም ዘበኛ አልነበርውም ። ይህ ሀብታም ብዙ ገንዘብ እንዳለው ሰው ሁሉ ያውቃል ከአስፈላጊ በላይ ትርፍ ገንዘብ እንዳለው ይታወቃል እዚህ ቤት ነው መግባት ያለብኝ ብሎ በተመሳሳይ ቁልፍ በሩን ከፍቶ ወደ ቤት ውስጥ ገባ።
ሰፊ ግቢና ብዙ ክፍሎች ያሉት ቤት ነው። ወደዋናው ቤትም ገብቶ ካዝናውን ከፍቶ ሲመለከት,,,,,
ወርቅ እና አልማዝ እንድሁም ብዙ ገንዘብ አገኘ። ያገኘውን እቃ ይዞ ለመውጣት ሲል ሁሉንም መውሰድ የለብኝም ምክንያቱም ሽይሀችን አላህ ፍሩ ብለውናልና ምን አልባት ይህ ነጋዴ ዘካ ያላወጣ ከሆነ መጀመሪያ ከገንዘቡ ዘካ ማውጣት አለበት አለ ።
ካዝናው አጠገብ ተቀምጦ ያገኘውን መዝገብ ፊኖስ አብርቶ መመርመር ጀመረ። እንዳጋጣሚ በሂሳብ ጎበዝ ነበርና ገንዘቡን ቆጥሮ ዘካውን አሰበ። ሂሳቡን ሲያሰላ ብዙ ሰአት ወስዶበት ኖሮ የፈጅር (የሱብሂ) ሶላት ደርሷል። አላህን የመፍራት መጀመርያው ሶላት መስገድ ነውና ወደመታጠቢያ ክፍል ውስጥ በመግባት ውዱእ አደረገ። ለሶላት አዛን አደረገ።
የቤቱ ባለቤት አዛን በቤቱ ውስጥ ሲሰማ ግራ በተጋባ ስሜት እና ድንጋጤ ተነሳ ሚስቱም ተከትላዋለች። የሚያስገርም ነገር ነበር የተመለከተው ፋኖሱ በርቱአል የገንዘብ ማስቀመጫው ሳጥኑ ወለል ብሎ ተከፍቷል በአቅራቢአው አንድ ሰው አዛን ይላል። ሚስቱ በአላህ እምላለሁ እየሆነ ያለው ነገር ምንም አልገባኝ አለች። አዛኑን ከጨረሰ ቡሀላ ሰውየው ወደልጁ ቀርቦ ሰውየው ምን አይነት ጉደኛ ነህ ማነህ አንተ ሌባ አለው።
ልጁም ፈርጠም ብሎ መጀመርያ ሶላት እንስገድና ከዛ ቡሀላ እናወራለን ይለዋል። ባለቤቱም ውዱእ አደረገ ልጁም ለባለቤቱ በል ቅደም ቅደምና አሰግደን ኢማምነት ለባለቤት ነውና አለው። ባለቤቱም ምን አልባት መሳርያ ይኖረዋል ብሎ ስለፈራ ኢማም ሁኖ አሰገደ። እንደት እንደሰገደ ግን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው። ሶላት ሰግደው እንደጨረሱ ባለቤቱ ወደልጁ በመዞር ማነህ ምን እያደረክ ነው ያለኸው? ጉዳይህ ምንድነው ሲል የጥያቄ ውረጅብኝ አወረደበት። ልጁም,,,,,,,,,,
ልጁም ያላወጣኸውን የዘካ ገንዘብ ሂሳብ እያሰላሁልህ ነበር የስድስት አመት ዘካህን አስቤ ጨርሸልሀለሁ ይህን የዘካ ገንዘብ ለሚገባቸው ሰወች እንድትሰጣቸው ለብቻ አስቀምጨልሀለሁ አለው።
ባለቤቱም በመገረም ሌላ ጥያቄ ጠየቀ ለመሆኑ አንተ እብድ ነህ? ልጁም ይህን ያደረገበትን ምክንያት ከመጀመርያው ጀምሮ ለባለቤቱ አጫወተው። ነጋደውም የልጁን ታሪክ ካደመጠ ቡሀላ ሂሳቡ ትክክል እና ምንመ ያልጎደለው መሆኑን አረጋግጦ ወደሚስቱ ሄደ። የልጁንም ታሪክ በዝርዝር አጫወታት።
ይህ ነጋዴ አንድት ልጃገረድ ልጅ ነበረችውና ወደሌባው ልጅ ተመልሶ እንድህ አለው : ልጀን ብደርህና እና የሂሳብ ሰራተኛየና ፀሀፊየ ባደርግህ እናትህንም ደግሞ እኔ ጋር ባስቀምጣት እንድሁም አንተን በተጨማሪ በንግድ ሽርክና ባስገባህ ደስ ይልሀል? ልጁም እሽ እቀበላለሁ አለ። እንደነጋም ነጋዴው ምስክሮችን ጠራና ኒካሁን አሰር የጋብቻ ስነስረአት ተደረገ። የነጋደው ሴት ልጅና ሌባው ተጋቡ።
አላህን በቁረአኑ አላህን የፈራ እሱ መውጫ ያበጅለታል። እርዚቅም ካላሰበበት ያመጣለታል ይለናል። ለዚህም ነው ይህ ወጣት አላህን ፈራ ካላሰበበት እርዚቅ አመጣለት። በማጭበርበር በስርቆት በማታለል እሚመጣ ነገር የለም ቢመጣም ለግዜው ይመስለናል እንጅ መጨረሻው ውርደት ነው አላህ የተቅዋ ሰወች ያድርገን
ፀሀፊ✍ አረቡ ዩሱፍ
✍ምንጭ ቀሶስ ኢማኒያት ከሚለው
መፅሀፍ የተወሰደ
#ረመዳን_23_ቀን_ቀረው🥰
@yasin_nuru @yasin_nuru
BY ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
Share with your friend now:
tgoop.com/yasin_nuru/5115