tgoop.com/yasin_nuru/5209
Last Update:
*⭐️ይህ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ታላቅ ምክር ነው።*
*አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋ መጣና "ለዱንያም ሆነ ለአኼራ *የሚጠቅም ንግግር ለመጠየቅ መጣው" አላቸው ።*
*እሳቸውም ደግሞ "የመጣልህን ጠይቅ"*
*አሉት።*
*⭐️"ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው?"*
*እሳቸውም "አላህን ፍራ" አሉት*
*⭐️ "ከሰው ሁሉ ሀብታመ* *ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው።*
*"ባለህ ነገር ተብቃቅተ አላህን አመስግን" አሉት*
*⭐️"ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል*
*"ለራስህ የምትወደውን* *ለሰዎች ውደድ"*
*አሉት።*
*⭐️ "ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል*
*"በአላህ ተወከል"አሉት*
*⭐️ "በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን*
*እፈልጋለው" ሲላቸው?*
*"ዚክር አብዛ" አሉት።*
*⭐️ "ከሰው ሁሉ በላጭ* *ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን*
*እፈልጋለው?" ሲል*
*"ለሰው ጠቃሚ ሁን" አሉት።*
*⭐️"የተከበረና ቸር ሰው* *ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው*
*"ችግርህን ለፍጡር አትንገር" አሉት።*
*⭐️"ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ *እፈልጋለው?" ሲል*
*"አንተም እነሱ የወደዱትን*
*ውደድ" አሉት::*
*⭐️"ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህንመገናኘት እፈልጋለው" ሲል*
*"ጀናባህን በደንብ ታጥበ* *እስቲግፋር አብዛ ማልቀስ* *መተናነስ መታመም*
*አለብህ" አሉት።*
*⭐️ "ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው"*
ሲላቸውም*
*"አላህን ልክ እንደምታየው ሁነክ ተገዛው" አሉት።*
*⭐️"ኢማኔ እንዲ ሞላ*
*እፈልጋለው" ሲል*
*"ፀባይህን አሳምር" አሉት።*
*⭐️"እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው" ሲል*
*"ተዋዱዕ አዘውትር" አሉት።*
*⭐️"ዱዓዬ ሙስተጃብ እንዲሆንልኝ እፈልጋለው?" ሲላቸው*
*"ሀራም አትብላ" አሉት::*
*⭐️ "አላህን ከሚታዘዙ ሰዎች ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል*
*"ግዴታዎችህን ፈፅም" አሉት።*
*⭐️"በአላህ ዘንድ ትልቁ ሀሠና ወይም ደግ ሥራ የቱ ነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው*
*"መልካም ፀባይ መተናነስ እና *በበላ ላይ ሰብር ማድረግ ነው" አሉት።*
*⭐️"በአላህ ዘንድ የትኛው ስርዓት ነው መጥፎ ሥራ?" ሲል ሲጠይቃቸው*
*"መጥፎ ፀባይና ፍላጎትን መከተል ናቸው" አሉት*
*⭐️"በዱንያም ሆነ በአኼራ የአላህን ቁጣ የሚያበርድ ምንድነው" ሲል ጠየቃቸው?
*"ድብቅ ሰደቃ እና ዘርን መቀጠል ናቸው" አሉት።*
*⭐️ "የቂያማ ቀን በአላህ ኑር ለመሰብሰብ*
*እፈልጋለው?" ሲል*
*"ሰውን አትበድል" አሉት*
*⭐️"የቂያማ እለት አላህ* *እንዲያዝንልኝ እፈልጋለው?"*
*"ለአላህ ባርያዎች እዘን" አሉት።*
*〰 "የቂያማ ቀን የጀሀነም እሳት የሚያጠፋው ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው*
*"በችግር ላይ ወይም በሙሲባ ላይ ትህግስት መሰድረግ ነው" አሉት።*
*⭐️ "የቂያማ እለት ነውሬ* *እንዲሸፈንልኝ እፈልጋለው?" ሲል*
*"የወንድምህን አይብ ሸፍን" አሉት።*
*⭐️"የቂያማ ቀን ከአላህ ቁጣ ሰላም ለመሆን*
*እፈልጋለው?" ሲል*
*"በአንድም ፍጡር አትቆጣ" አሉት።*
*አሏህ ሱብሃን ወተአላህ ባወቅነው በስማነው የምንስራ ያድርገን ኣሚን!**
SHARE 🔗SHARE
JOIN: @yasin_nuru
JOIN: @yasin_nuru
BY ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
Share with your friend now:
tgoop.com/yasin_nuru/5209