tgoop.com/yasin_nuru/5210
Last Update:
" የነብያችን ﷺ ስም በክፉ ነገር ሲነሳ ነፍስያችንን መቆጣጠር ያቅተናል ፤ ሰብር ያሳጣናል። ሆኖም የምናደርገው ነገር ቢኖር ተንኳሾችን ለህግ እና ለህግ ማቅረብ ብቻ ነው " - ፌዴራል መጅሊስ
የፌዴራል መጅሊስ በእስልምና ሃይማኖት ላይ ትንኮሳ ፈጽሟል / በነብዩ ሙሀመድ ﷺ ላይ ክብረነክ ፀያፍ ንግግር አድርጓል ያለውን ግለሰብ ወደ ህግ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።
መጅሊስ ፤ " ህግና ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ ክስ መስርተን እየሄድን ነው " ያለ ሲሆን ምዕመኑ " በትዕግስት ዱአ በማድረግ እንዲጠብቅ ብሏል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ምን አሉ ?
" ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከሁሉም በላይ ከማንም በላይ ከራሳችንም በላይ የምንወዳቸው እና የምናከብራቸው እስልምናችን እሳቸውን ካልወደድን እና ካልተቀበልን መኖር የማይችል ከነፍስያችን በላይ ህይወታችንን ለእሳቸው የምንሰጥ ነብያችን ስም በክፉ ነገር ሲነሳ ነፍስያችንን መቆጣጠር ያቅተናል ፤ ሰብር ያሳጣናል።
ሆኖም ግን የምናደርገው ነገር ቢኖር እንዲህ ያለ ተንኳሾችን የምናቀርበው ለህግ እና ለህግ ብቻ ነው። ህግ ባለበት ሀገር ለህግ ነው የምናቀርበው።
መጅሊሳችን ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ሁለት ነገር ሰርቶ አሳልፏል። አንድ እንዲህ ያለ ትንኮሳ የማንቀበል መሆኑን እንደ ሙስሊም በሰፊ አውግዘናል ፤ ምንም ግለሰብ ቢሆንም። በሌላ በኩል መጅሊስ ህግና ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ ክስ መስርቶ እየሄደበት ነው። መንግሥትም ቢሆን እየተናበብን እየሄድን እንደሆነ እያየን ነው።
ሀገር ለማበላሸት፣ አንድነትን ለማናጋት የሚተጋውን ትንሽ ቦታ ስለምትበቃ እስከዛሬ ተደብቆ ቢኖርም ነገ ከነገወዲያ መያዙ አይቀርም ኢንሻ አላህ ወተአላ። ስለዚህ እሱ ተይዞ በስርዓት ለፍርድ እስከሚቀርብ ድረስ ከኛ የሚጠበቀው በትዕግስት ዱአ እያደረግን መጠበቅ ነው።
በተለይ እኛ የሃይማኖት ተቋማት ደግሞ እንዲህ አይነት ትንኮሳ የሚፈጽሙት ሃይማኖትን ወክለው አይደለም፣ ተቋማትን ወክለው አይደለም፣ ተቋማት ልከዋቸው አይደለም፣ የተቋማትን ኃላፊነት ወስደው አይደለም የግል ትንኮሳ ነው። የግል ትንኮሳ ሰላም እንዲደፈርስ የማይሰራ ስራ ስለሌለ ይሄን ተከትለን እኛ አብሮነታችን፣ ትላንትና የነበረ የጋራ የአብሮ መተባበር ተጠናክሮ ይቀጥላል እንጂ እንደ ተንኳሾቹ ይሻክራል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችኃል።
ማንም ይሁን ማንም የትኛውንም ሃይማኖት ወክሎ የተነገረ ስላልሆነ የግል ሚናው ስለሆነ በግሉ ባደረገው ዋጋ መጠን እርምጃ ይወሰድበታል እርምጃ ስንል ህጋዊ እርምጃ ማለት ነው " ብለዋል።
Tikvah
SHARE 🔗SHARE
JOIN: @yasin_nuru
JOIN: @yasin_nuru
BY ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
Share with your friend now:
tgoop.com/yasin_nuru/5210