tgoop.com/yeabewu/3
Last Update:
ስለ ጸሎት ብሂለ አበው
✝ በእንተ ጸሎት ብሒለ አበው ✝
❖ ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ፀሎትን የማደታደርግ ነፍስ ሕይወት የላትም፡፡
/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
❖ የተቆጣ ሰው ጸሎት የረከሰና ተቀባይነት ያጣ ዕጣን ነው፡፡ የተቆጣ ሰው መሥዋዕት ተቀባይነት የለውም ፡፡ ቁጣ የዕብደት ድርጊት ነው ፡፡ ሰዎችን እንደ አውሬዎች ያደርጋቸዋል ••••• የተቆጣ ሰው ዐይኖቹ በደም የተሞሉ ጥፉዎች ናቸው ፡ የጨዋሰው ፊት ግን ብሩህ ሲሆኑ ዐይኖቹም በክብር ይመለከታል ፡፡
/ ማር አውሳረስ/
❖ ሌሊት እግዚአብሔርን ለማመስገን የፈተጠረ ልዩ ጊዜ ነው ፡፡
/ ቅዱስ አባ ይሰሕቅ /
❖ ከንቁሕ፡ ከትጉሁ ልቡና ጋር ያለ ፀሎት የጦር ዕቃ ነው ፡፡ ነፍስ ከአግዚአብሔር አንድ ከሆነች የተጋች የነቃች ከሆነች ወደ እግዚአብሔር የምትመለከት ከሆነች ኀብረቷ እግዚአብሔርን ጋር ብቻ ይሆናል፡፡
/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
❖ ንጽሕ ጸሎት ምንድን ነው ? ተብሎ ተጠይቆ ሲመለስ " ለዓለም መሞት ነው፡፡
/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ /
❖ ልጅ ከአባቱ አንደሚጫወት በፀሎት ከልዑል እግዚአብሔር ጋር ተጫወት ፡፡
/ ማር ይስሐቅ/
❖ በእግዚአብሔር ፊት ለጸሎት ስትቆም ልክ የእሳት ፍም አጠገብ እንደቆምክ አስብ፡፡
/ ታላቁ መምህር ይስሐቅ /
❖ ዕንባሕን ከመፍሰስ እንዲያቆም ከወደድህ ዘወትር ኃጢአትህን እያሰብህ በፀሎት ጽሙድ ሁን፡፡
/ ማር ይስሐቅ/
❖ ቅዱሣን አባቶቻችን እንደሚያደርጉት አንድን ችግር በእግዚአብሔር ፊት በማስቀመጥ ፡ በመጸለይና በመጾም መፍትሔ ማግኘት ይቻላል፡፡
/ ዮሐንስ አፈወርቅ/
❖ የጻድቃን መባቸው የንሰሐ እንባ /የዓይኖቻቻው እንባ / ነው ፡፡
/ ማር ይስሕቅ/
❖ ኃይለኛ መድኃኒት መርዘኛ ፍጥረታትን ነቀሎ እንደሚያወጣ ጸሎትም ክፉ ሐሳቦችን ነቀሎ ይጥላል፡፡
/ እማሆይ ሰንቅሊጢቃ/
❖ በአንተ ላይ ክፍ በሠራብህ ወንድም ላይ ለበቀል የሠነዘርከው ነገር ሁሉ በጸሎት ጊዜ በልቡናህ እየመጣ ይፈትንሃል ፡፡
/ አባ ኔለስ/
❖ ጸሎት የደግነት ፍሬ : የቁጣም አለመኖር ነው ፡ ጸሎት የትካዜና የውስጣዊ ሐዘን ማስታወሻ ነው ፡፡
/ አባ ኔለስ/
❖ ነገሮች ሁሉ አንተ እንደምትፈልጋቸው እንዲሆኑ አትመኝ እግዚብሔርን እንደሚያስደስቱት እንጂ እንደዚህ ከሆነ የማትታወክ በጸሎትህም ጊዜ አዘውትረህ የምታመስግን ትሆናለህ ፡፡
/ አባ ኔለስ/
❖ በምስጋና ቃል እግዚአብሔርን እንደሚያመሰግኑት አንሁን ፡ ዜማ የሚያመሰግኑ አሉ ፡ የሚዘምሩም አሉ በልብ የሚያመሰግኑ አሉ ፡፡
/ ቅድስ አትናቴዎስ /
❖ ከእራት በኋላ ያለው ጊዜ ምስጋና ጊዜ ነው ፡፡
ምስጋናን የሚቀረብ ደግሞ ንቁና የተረጋጋ ይሆናለሁ ፡፡
ከእራት በኋላ ወደ ፀሎት እንጂ ወደ መኝታ እንሂድ ፡፡
ያለበለዚይ ግን በደመ ነፍስ ከሚመሩት አውሬዎች የበለጠ በደመ ነፍስ የምንመራ እንሆናለን ፡፡
/ ዮሐንስ አፈወርቅ/
መልካም ቀን ይሁንልን
@yeabewu
BY የአባቶች ሃይማኖት
Share with your friend now:
tgoop.com/yeabewu/3