tgoop.com/yeabewu/7
Last Update:
እንደ እባብ ጠቢብ ኹን
እንደ እባብ ጠቢብ ኹን ሲል ምን ማለት ነው? እባብ ጭንቅላቱን (ራሱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱ እጅግ በጣም ብዙ ጉዳት ቢደርስበት ይመርጣል፡፡
ስለዚህ እንደ እባብ ጠቢብ ኹን ሲልህ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን፣ ዝናህን፣ ጓደኞችህን፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ማጣት ካለብህ እንኳን በዚህ ማዘን መቆርቆር የለበህም ሲል ነው፡፡ ሃይማኖትህ ራስህ ነውና - እውነትን የምታውቅበት! እውነት ደግሞ አርነት ያወጣሃል፡፡
ኾኖም እንደ እባብ ጠቢብ መኾን ብቻውን ለእኛ በቂያችን አይደለም፤ እንደ ርግብ ሐቀኞችና የዋሆች መኾንም ያስፈልገናል፡፡ በጎ ምግባር የሚኖረው ጥበብንም የዋህነትንም አስተባብሮ መያዝ ሲቻል ነውና፡፡ ለምን ቢሉ እንደ እባብ ጠቢብ የኾነ ሰው ስለ ሃይማኖቱ ሲል ብዙ መከራዎችን ሊቀበል ይችላል፡፡
መከራ በሚያደርሱበት ላይ ክፉን በክፉ አለመመለስ የሚችለው ግን እንደ ርግብ የዋህ መኾን ሲችል ነው፤ እንደ ርግብ የዋህ መኾን ማለት መከራ በሚያደርሱብን ላይ በበቀል አለመነሣሣት መቻል ማለት ነውና፡፡ የዋህነት በጥበብ ሚዛን ካልተመጣጠነ አንድ ሰው መከራ ሲቀበል መከራ በሚያደርስበት ላይ በበቀል እንዲነሣ ያደርጓልና፡፡ ጥበብ በየዋህነት ሚዛን ካልተመጣጠነም እንደዚሁ አላስፈላጊ ሰማዕትነትን እንዲቀበሉ ያደርጋልና፡፡
ስለዚህ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል እንደ እባብ ጠቢብ ኹን፡፡ አብረህም መከራ በሚያደርስብህ ላይ ላለመበቀል ስትል እንደ ርግብ የዋህ ኹን፡፡ ኹለቱንም አዋሕደህ አስተባብረህ ያዝ!
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@yeabewu @yeabewu
@yeabewu @yeabewu
@yeabewu @yeabewu
BY የአባቶች ሃይማኖት
Share with your friend now:
tgoop.com/yeabewu/7