Telegram Web
🥰9
🕊                     💖                     🕊


[  ❝ ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕይት የሰርግ ቤት ናት ❞  ]

🕊                     💖                     🕊

❝ የሐዲስ ኪዳኑ ታላቅ ሰርግ የተፈጸመባት ሰርግ ቤት በቃና ዘገሊላ የታደመችው እመቤታችን ናት፡፡ ይህቺን የሰርግ ቤት ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ፦ ❝ ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕይት የሰርግ ቤት ናት። ❞ በማለት ሲያመሰግናት አባ ሕርያቆስ ደግሞ በቅዳሴው ፦ ❝ የሚልክያስ ንጹሕ አዳራሽ ❞ በማለት በ ታላቅ አዳራሽ መስሎ ይገልጻታል፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ስለ ጌታችን ፦ ❝ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል። ❞ በማለት እልፍኝ ከተባለችው እናቱ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ [ ውዳ.ማር ፤ ቅዳ.ማር. ፤ መዝ.፲፰፥፭ ]

ሰርግ ቤት ❞ በተሰኘችው እመቤታችን በሰርግ ቤት ውስጥ የሚከናወኑ አራት ነገሮች ተፈጽመዋል፡፡

❝ በሰርግ ቤት ውስጥ ሙሽራውና ሙሽሪቱ አንድ ሆነው እንደሚዋሐዱ በእመቤታችን ውስጥም መለኮትና ሥጋ አንድ ሆነዋል፡፡ በሰርግ ቤት የሙሽራውና የሙሽሪት ዘመዶች አንድ ቤተሰብ እንደሚሆኑ በእመቤታችን ማኅጸን በተፈጸመው የአምላክና ሰው ተዋሕዶ ምክንያት ሰውና መላእክት ፤ ነፍስና ስጋ ፤ ሕዝብና አሕዛብ አንድ ሆነዋል፡፡

በሰርግ ቤት መብልና መጠጥ እንደሚቀርብ በእርስዋ በተደረገው ተዋህዶ ምክንያት ሥጋወደሙ ለሁላችን ማዕድ ሆኖ ተሰጥቷል፡፡

በሰርግ ቤት ዘፈንና ጨዋታ እንዳለ ደግሞ ሁሉን የሚያስደስቱ ታላላቅ ተአምራት በአምላክ ሰው መሆን ምክንያት ታይተዋል፡፡ ❞ [ ውዳ.ማር.ትር.ገጽ ፶፪ ]

[    ቃና ዘገሊላ    ]


†                       †                       †
💖                    🕊                    💖
👍1
3
🕊                      💖                      🕊

[  ለማያምኑት አልቅሱላቸው ! ]

🕊                      💖                      🕊


❝ ለማያምኑት አልቅሱላቸው የጥምቀትን ማኅተም ሳያገኙ ለሞቱት አልቅሱላቸው። እነርሱ ከመንግሥተ ሰማያት ውጭ ናቸውና ልናለቅስላቸው ይገባናል። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም ተብሏልና።

ጥምቀትን ለኃጢአት ሥርየት ሰጠን እንዲሁም በዚሁ በጥምቀት ከፍዳ እንድንድንና መንግሥቱን እንድንወርስ አደረገን ❞

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ]

🕊                      💖                      🕊

❝ ማንም ሰው ካልተጠመቀ በቀር መዳንን አያገኝም ፤ በውኃ ሳይሆን በደማቸው ከተጠመቁ ከሰማዕታት በስተቀር። ጌታችን ዓለምን በመስቀሉ ባዳነ ጊዜ ጎኑን ተወጋ ፣ ያን ጊዜም ደም እና ውኃ ከጎኑ አፈለቀልን። ይህም በሰላም ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች በውኃው ይጠመቁ ዘንድ ፣ በስደትና በመከራ ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በደማቸው ይጠመቁ ዘንድ ነው።

ሰማዕትነትን ጌታችንም ጥምቀት ብሎታል ፤ እንዲህ ሲል - እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ፣ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ፍቅር ደማቸውን በማፍሰስና ስለ እርሱ መከራ በመቀበል የእምነታቸውን ምስክርነት በደማቸው ይሰጣሉና።❞

[ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ]


🕊                      💖                      🕊
👍3❤‍🔥11
13
🕊

[ † እንኩዋን ለጻድቃን ቅዱሳን አቡነ ዘርዓ ቡሩክ እና ፯ቱ ደቂቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  አቡነ ዘርዓ ቡሩክ †  🕊

ሃገራችን ኢትዮዽያ :-

- ብሉይ ከሐዲስ ያልጐደለባት
- በክርስቶስና በድንግል እናቱ ኪደተ እግር የተቀደሰች
- የቅዱሳን መጠጊያ እና
- ብዙ ቅዱሳንን ከእቅፏ ያፈራች ስለ ሆነች የተባረከች ሃገር ትባላለች::

- ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ቅዱሳንን አፍርተዋል:: በምሥራቅም: በምዕራብም: በሰሜንም: በደቡብም ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የቅዱሳን ቤቶች ናቸው:: ቅዱሳንን በብዛት ካፈሩ አካባቢዎች አንዱ ደግሞ ምድረ ጐጃም ነው::

- በጐጃም አካባቢ ከተነሱ ቅዱሳን ደግሞ አንዱና ስመ ጥሩ ጻድቅ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ናቸው:: አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጐዳና የተለዩ አባት ናቸው:: ለመጥቀስ ያህል እንኩዋ :-

፩. በታሪክ ዓለምን ከበው የያዙ ፪ቱ ግሩማን አራዊት [ብሔሞትና ሌዋታንን] ጥርስ ቆጥረው: ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል:: [በነገራችሁ ላይ ይህ ጉዳይ ዛሬም ድረስ ሳይንሱ በብዙ ድካም ያልደረሰበት ነው]

፪. ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል:: ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል::

፫. መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ቅዱስ ኢያሱ በገባኦን ፀሐይን አቁሟል:: ዘርዓ ቡሩክ ግን በጥበበ እግዚአብሔር ፀሐይን ለ፭ ዓመት አቁመዋል::

፬. ጻድቁ ከንጽሕናቸው ብዛት ፲፪ ክንፍ [መንፈሳዊ ክንፍ] ተሰጥቷቸው ነበር:: ከዚህ በተረፈም በጾም: በጸሎት: በትርምትና በስብከተ ወንጌል ፍጹም ጽሙድ ነበሩ::

- ጻድቁ የተወለዱት በ፲፮ኛው መቶ ክ/ዘመን እዚያው ጐጃም ውስጥ ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ: እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ:: ወላጆች በልጅ እጦት ተማለው ይህን የተቀደሰ ፍሬ አገኙ:: "ጸጋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ከኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቷቸዋልና::

- ቀጥሎ የወለዱትንም "ተስፋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ይህም የጻድቁ ታናሽ ወንድም ነው:: በሒደት ግን የጸጋ ኢየሱስ ስም በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ዘርዓ ቡሩክነት ተቀይሯል:: ጻድቁን ስመ ጥር ካደረጉዋቸው ሥራዎቻቸው መካከል በአፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩት ቅድሚያውን ይወስዳል::

- ነገሩ እንዲህ ነው:: በ፩ ሺህ ፭ መቶ ፺፰ [1598] ዓ/ም በኢትዮዽያ ላይ የነገሡት አፄ ሱስንዮስ ዼጥሮስ ፓኤዝ [ፔድሮ ፓኤዝ] ከሚባል ፈረንጅ መናፍቅ ጋር በፈጠሩት ወዳጅነት ሃይማኖታቸውን ለወጡ:: ካቶሊክ [ሮማዊ]ም ሆኑ::

- በሁዋላም አልፎንሱ ሜንዴዝ የሚሉት እሾህ መጥቶ ሁሉም የኢትዮዽያ ሕዝብ መናፍቅ እንዲሆን ከንጉሡ ጋር መከረ:: ለጊዜው በቤተ መንግስቱ አካባቢ የነበሩ መሣፍንት ተቀላቀሉ:: እየቆየ ግን ዜናው በመላ ሃገሪቱ ተሰማ::

- በተለይ በ፩ሺህ ፮ መቶ ፲፩ [1611] በተዋሕዶ አማኞችና በመናፍቁ ንጉሥ መካከል ነገሩ ተካሮ ዻዻሱ አቡነ ስምዖን ጠዳ ላይ መገደላቸው ተሰማ:: በዚህ ጊዜ ገበሬው ከእርሻው: ሴቷ ከማዕድ ቤት: ካህኑ ከመቅደሱ: ነጋዴው ከገበያው እየወጡ ስለ ቀናችው ሃይማኖት ደማቸውን አፈሰሱ::

- በበዓት የተወሰኑ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳንም ወጥተው ተሰየፉ:: በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ:: ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጣሉት::

- ተሻግረውም ከንጉሡ አደባባይ ደንቀዝ ደረሱ:: በጊዜውም ልክ እንደነ ፍቅርተ ክርስቶስና ወለተ ዼጥሮስ እርሳቸውም መከራ ደረሰባቸው:: ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ:: በጨለማ እስር ቤትም ፭ ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር::

- እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም:: ከ፭ ዓመት በሁዋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል:: ዘርዓ ቡሩክም ከእሥር ተፈትተዋል::
- እግዚአብሔርም በከሐዲው ንጉሥ ላይ ፈርዶ ፋሲል ነግሷል: ሃይማኖት ተመልሷል:: ጻድቁም በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል::

- ጐጃም ሲደርሱም ሰይጣን እርሳቸውን መስሎ ሲያስት ስላገኙት ወደ ጥልቁ አስጥመውታል:: በተረፈ ዘመናቸው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ብዙ ተጋድለው ጥር ፲፫ ቀን ዐርፈዋል:: ታኅሳስ ፲፫ ቀን ልደታቸው ነው::

" ድንቅ ሠሪ አባት ናቸውና ዛሬም በግሺ ብዙ ተአምራት ይደረጋሉ "


🕊  † ቅዱሳን ፯ [ 7 ]ቱ ደቂቅ †  🕊

እነዚህ ፯ ቅዱሳን ከዘመነ ሰማዕታት እስከ ዘመነ ጻድቃን የተዘረጋ ታሪክ አላቸው:: ፯ቱም ባልንጀሮች ሲሆኑ በ፪ኛው መቶ ክ/ዘመን በኤፌሶን ተወልደው አድገዋል:: ክርስትናን ተምረውም በወጣትነታቸው የንጉሥ ጭፍሮች ሁነዋል:: የተቀጠሩትም የቤተ መንግስቱን ግምጃ ቤት ለመጠበቅ ነው::

- በሥራቸውም ሆነ በጠባያቸው ደጐች ነበሩና ንጉሡ ዳኬዎስም: ሕዝቡም ይወዷቸው ነበር:: እነርሱ ግን በጉብዝና ወራት ፈጣሪን ማሰብን መርጠው በፍቅር: በጸሎትና በምጽዋት ይተጉ ነበር:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ ግን ጭንቅ መከራ መጣ::

- ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስትናውን ትቶ ጣዖት አምላኪ ሆነ:: አዋጅም አስነገረ:: አዋጁም "ክርስቶስን ያልካደ: ለጣዖትም ያልሰገደ: ሃብት ንብረቱ ለዘረፋ: እጅ እግሩ ለእስር: ደረቱ ለጦር: አንገቱ ለሰይፍ: ቤቱም ለእሳት ይሰጣል" የሚል ነበር:: በዚህ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ::

- የበርካቶቹም ደማቸው ፈሰሰ:: ኤፌሶን የግፍና የአመጻ ከተማ ሆነች:: የመከራ ጽዋው ጊዜውን ጠብቆ ወደ ፯ቱ ወጣቶች ዘንድ ደረሰ:: ንጉሡ እነሱንም አስጠርቶ "ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: እነርሱ ግን የአምላካቸውን ፍቅር በዋዛ የሚቀይሩ አልነበሩምና "እንቢ" አሉት::

- ንጉሡ ምንም ክፉና አውሬ ቢሆንም ይወዳቸዋል:: ሊገድላቸው አልፈለገምና አሳሰራቸው:: ከቀናት በሁዋላ አስጠርቶ ሊያታልላቸው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: በዚያ ወራት ጦርነት ይበዛ ነበርና ግዛት ለማስፋትም ቢሉ ለማስገበር ዳኬዎስ ወጣ::

- ከመውጣቱ በፊት ግን ፯ቱን አስጠርቶ "አሁን ከእስር ፈትቻቹሃለሁ:: ከጦርነት እስክመለስ ከልባችሁ ጋር ምከሩ:: ካልሆነ ሞት ይጠብቃቹሃል" ብሏቸው ነበር የወጣው:: ቅዱሳኑ ንጉሡ እንደ ወጣ ተቀምጠው መከሩ:: ውሳኔንም አስተላለፉ::

- ዓለምን ንቀው: ሃብት ንብረታቸውን መጽውተው: ትንሽ ሳንቲም ብቻም ይዘው በድብቅ ወጡ:: አንድ ወታደር [በጐች አሉት] ይከተላቸው ነበርና የት እንደ ገቡ ተመለከተ:: ቅዱሳኑ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት በበዓታቸው ውስጥ ይተጉ ነበር:: ከእነሱም አንዱ በተራ እየወጣ ቂጣ ይገዛ ነበር::

- አንድ ቀን ግን ከእነሱ አንዱ ራት ሊገዛ ሲወጣ ንጉሡ መመለሱን ሰማ:: ወደ በዓቱ ተመልሶ ለወንድሞቹ ነገራቸው:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ፯ቱም አልወጡም:: በዓታቸውን ዘግተው ሲጸልዩ ደክሟቸው ተኙ:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ግን አልነቁም::

- ያ የበጐች ባለቤት [ወታደር] ለብዙ ቀናት አለመውጣታቸውን ሲመለከት "ሙተዋል" ብሎ አዘነ:: በድብቅ ክርስቶስን ያመልከው ነበርና:: እርሱ የቅዱሳኑን ተጋድሎ በድንጋይ ሰሌዳ ላይ ጽፎ ወደ በዓታቸው ውስጥ ጣለው::

- ትልቅ ድንጋይም አምጥቶ ገጠመው:: እነዚህ ቅዱሳን ተኝተዋልና አልነቁም:: ቀናት: ወራት: ዓመታት ተዋልደው ለ፫፻፸፪ ዓመት ተኙ:: አንድ ቀን አንድ እረኛ ለሥራ ፈልጐት ድንጋዩን ፈነቀለው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳኑ ነቁ::
4
- በወቅቱ መልካቸው የወጣት ነው:: እድሜአቸው ግን ፬ መቶ ሊሞላ ትንሽ ቀርቶት ነበር:: ልክ እንደ አቤሜሌክ ብዙ መተኛታቸው አልታወቃቸውምና ከመካከላቸው አንዱ የራት ዳቦ ሊገዛ ቢወጣ ግራ ተጋባ:: ኤፌሶን የማያውቃት ሌላ ሃገር ሆነችበት:: ከተማዋ ዘምናለች::

- በየቦታው አብያተ ክርስቲያናት: ቅዱስ መስቀልም በየአደባባዩ ተተክለዋል:: ነገሩ ግር ቢለው አንዱን ከመንገድ ጠርቶ "ወንድሜ! ይህቺ ከተማ ኤፌሶን አይደለችምን?" አለው:: እርሱም "አዎ ናት" ብሎት አለፈ::

- ችግሩ ግን "ራት ልግዛ" ብሎ ወደ ገበያ ሲሔድ: እርሱ የያዘው ገንዘብ የዳኬዎስ ስም የተጻፈበት መሆኑ የፈጠረው ነበር:: በነጋዴዎቹ "የተደበቀ የጥንት ገንዘብ አግኝተሃል" በሚል ተከሶም ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ዘንድ ቀረበ:: [ትንሹ ቴዎዶስዮስ ነው:: የነገሠውም በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው]

- በክርክሩ መካከል ቅዱሱ የእሱንና የወንድሞቹን ነገር ሲናገር ንጉሡም: ሊቀ ዻዻሱም [አባ ቴዎድሮስ ይባላል] ተገረሙ:: አብረው ከከተማ ወጥተው ሔደው: ፯ቱንም ሲጸልዩ አገኟቸው:: ፊታቸውም እንደ እግረ ፀሐይ ያበራ ነበር:: ፯ቱም ለ፯ ቀናት በኤፌሶን ድውያንን እየፈወሱ: ሰውን ሁሉ እየባረኩ ቆዩ::

- ይህ ሁሉ የተደረገው በወቅቱ "ትንሳኤ ሙታን የለም" የሚሉ መናፍቃን ተነስተው ብዙ ሰው ክዶ ነበርና ለእነሱ ምሥክር ሊሆንባቸው ነው:: በርካቶችም በዚህ ድንቅ ተስበው ወደ ሃየማኖት ተመልሰዋል:: ፯ቱ ቅዱሳን ግን በ፯ኛው ቀን በክብር ዐርፈዋል:: ንጉሡ ፯ የወርቅ ሣጥኖች ቀብሯቸዋል::

አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

🕊

[ † ጥር ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ኢትዮዽያዊ [ እረፍታቸው ]
፪. ሰባቱ ደቂቅ ቅዱሳን [ ከኤፌሶን ]
፫. ቅዱስ አባ ነካሮ
፬. ቅዱስ ቃሮስ

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
፫. ቅዱስ አስከናፍር
፬. "፲፫ ግኁሳን ጻድቃን"
፭. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ
፮. ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት

" በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ:: ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል:: የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ : የእግዚአብሔርም ፍቅር : የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" [፪ቆሮ.፲፫፥፲፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2👍1
Audio
2
5👍1
#ምትክ_የለሽ_ተአምር

ጌታችን ውኃውን ወደ ወይን በመቀየር እውነተኛዋ ሰርግ ቤት ቤተክርስቲያን ጣፋጭ ሕይወት የሚቀዳባት ባለጸጋ አደረጋት።
በለስ የጎደለባትን ገነት በወይን ሐረግ አሸበረቃት።
ሰው ማጉደልን ገንዘብ ቢያደርግ ጉድለትን የሚሞላ
#አምላክ_በሥጋ ተገለጠ።
ውኃው ይዘቱን ሳይለውጥ ወይን እንደኾነ አካላዊ ቃል ባለመለወጥ ሰው ኾነ።
ሙሴ ውኃውን ወደ ደም በመለወጥ ዘመነ
#መርገምን አረጋገጠ።
#ክርስቶስ ውኃውን ወደ ወይን በመቀየር ዘመነ #ምሕረትን ገለጠ።

#መልካም_ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
11🙏2🔥1
🕊                      💖                      🕊

❝ አባትህን ጠይቅ ፥ ያስታውቅህማል ፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ ፥ ይነግሩህማል። ❞

[ ዘዳ.፴፪፥፯ ]

🕊                      💖                      🕊

[ እግዚአብሔርን ባለማወቅ ፣ ፈቃዱንም ባለማስተዋል ፣ በክህደት ፣ በኑፋቄ ፣ በአመጻ ሥራና ይህን በመሰሉ ጥንተ ጠላት በሚያስነሳቸው የጥፋት ነፋሳትና ማዕበላት ተወስደን እንዳንጠፋ ደገኛዋን ጥበብ የሚያስተምሩን አባቶች ሊቃውንትን በዘመኑ ሁሉ የሚሰጠን የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመሥገን። ]

❝ ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። ❞ [ ፪ቆሮ.፱፥፲፭ ]


†                       †                       †
💖                    🕊                     💖
7
2025/07/13 04:04:10
Back to Top
HTML Embed Code: