tgoop.com/Esat_tv1/20835
Last Update:
ወደ ሀገር አቀፍ የቁርኣን ሒፍዝ ውድድር በታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር 5 ሲመጡ ምዕመናን ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦች‼️
👉የተለመደውን ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፈቃድ አስተባባሪዎች ፍተሻ ትብብር ማድረግ
👉የሰላት መስገጃ እና ጥላ ይዘው ይምጡ
ማንኛውም ለደህንነት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፈቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲያሳውቁ
👉የ CAR PASS ያላቸው ተሽከርካሪ ይዘው የሚመጡ የዝግጅቱ ታዳሚያን ጊዮን ሆቴል ጊቢ ውስጥ እና እስታዲየም አካባቢ መኪና እንዲያቆሙ::
👉የ CAR PASS ካላቸው እንግዶች ውጭ ተሽከርካሪ ይዘው የሚመጡ የዝግጅቱ ታዳሚያን በአቅራቢያ ባሉ በኮሪደር ልማቱ በተሰሩ አልያም ሌሎች ምቹ በሆኑ ስፍራዎች መኪና እንዲያቆሙ::
👉ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋራት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ እናደርጋለን:: ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል::
👉ከፕሮግራሙ አላማ ውጭ ማንኛውም ተግባር ተቀባይነት የሌለው መሆኑ
በከተማችን የትራንስፖርት ችግር መኖሩ የሚታወቅ በመሆኑ የግል ተሽከርካሪ ይዘው የሚመጡ የዝግጅቱ ታዳሚያን
👉ፆመኞችን ወደ ዝግጅቱ ሲመጡ እና ሲመለሱ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ትብብር ቢያደርጉ::
👉ለኢፍጣር የተዘጋጁ ምግቦችን ከመብልነት ውጭ መጠጦችን ከመጠጥነት ውጭ በመጠቀም ማባከን እና ከዝግጅቱ ዓላማ ውጭ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባራችንን ለሌሎች አርአያ በመሆን ማሳየት
@Esat_tv1
@Esat_tv1
BY ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

❌Photos not found?❌Click here to update cache.
Share with your friend now:
tgoop.com/Esat_tv1/20835